- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

የሕግ ሉዓላዊነት ፣ የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት አድልዎ እና የአህጉራዊ ፍትሕ መፃኢ እድል

የሕግ ሉዓላዊነት፣ የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት አድልዎ እና የአህጉራዊ ፍትሕ መፃኢ እድል
ሰብስክራይብ
''አይሲሲ የምዕራባውያን አጋሮች በሚፈጽሟቸው ጥፋቶች ላይ ግን እርምጃ ከመውሰድ ይቆጠባል። የሳህል ሀገራትና የቻድ ከሮም ድንጋጌ መውጣት የዚሁ መዋቅራዊ ችግርና አድሏዊ አሠራር ቀጥተኛ ውጤት ነው፤'' ሲሉ የሕግ ምሁርና ተመራማሪ መታገስ ውለታው ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፕሮግራማችን፤ ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት (ICC) ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በአፍሪካ እና በደቡብ ዓለም መሪዎች ላይ ያተኮረበትን መዋቅራዊ አድልዎ፣ የምዕራባውያን ከተጠያቂነት ነፃ መሆን እንዲሁም ከሕግ ኒዮ-ኮሎኒያሊዝም ወጥቶ የአፍሪካን የፍትሕ ሉዓላዊነትና የማላቦ ፕሮቶኮልን የማጠናከር ስትራቴጂዎችን በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት መምህር መታገስ ውለታው ጋር በጥልቀት ተወያይተናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0