- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

አህጉራዊ የጥራት ደረጃዎችና የአፍሪካ ነጻ ንግድ ቀጠና የንግድ ትስስር ማስፈጸሚያ ስርዓት

አህጉራዊ የጥራት ደረጃዎችና የአፍሪካ ነጻ ንግድ ቀጠና የንግድ ትስስር ማስፈጸሚያ ስርዓት
ሰብስክራይብ
''የአፍሪካ እውነተኛ የኢኮኖሚ፣ የቴክኖሎጂና የኢንዱስትሪ ሉዓላዊነት የሚረጋገጠው በቴክኖሎጂ፣ በሳይንሳዊ ስነ-ልክና የጥራት መሰረተ ልማት ራሷን ችላ መቆም ስትችል ብቻ ነው። በአህጉራችን ወጥ የሆነ የመለኪያና የጥራት መስፈርቶችን ማዋሃድና የሰው ኃይል አቅማችንን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ስንችል፣ በንግድ ማዕቀፎች ስም የሚመጡ አድሏዊ የሆኑ የውጭ የምስክር ወረቀት መስፈርቶችን መስበር እንችላለን'' ሲሉ የኢትዮጵያ ስነ-ልክ ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር አቶ ፍቅረአብ ማርቆስ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፖድካስት፤ በአዲስ አበባ ከተማ "ስነ-ልክ ለዲጂታል ሽግግር፡ የታመኑ ልኬቶች ለአፍሪካ የወደፊት እድገት" በሚል መሪ ቃል ከተካሄደው 19ኛው የአፍሪካ ስነ-ልካ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ጋር ተያይዞ፣ የአፍሪካ ነጻ ንግድ ቀጠናን በጉልህ ለመጠቀምና የኢንዱስትሪ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የመለኪያና የጥራት መሰረተ ልማት የሚያበረክተውን ወሳኝ ሚና ከኢትዮጵያ ስነ-ልክ ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር አቶ ፍቅረአብ ማርቆስ ጋር በጥልቀት ተወያይተናል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0