ደቡብ ሱዳን በጎረቤት ሱዳን ያለውን ግጭት በሰላም ለመፍታት የአስታራቂነት ሚና ለማወጣት ዝግጁ መሆኗን አስታወቀች

ሰብስክራይብ

ደቡብ ሱዳን በጎረቤት ሱዳን ያለውን ግጭት በሰላም ለመፍታት የአስታራቂነት ሚና ለማወጣት ዝግጁ መሆኗን አስታወቀች

​ ይህ የተገለጸው ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ከዳርፉር ገዢ ሚኒ አርኮ ሚናዊ ጋር በጁባ ካደረጉት ውይይት በኋላ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤታቸው ባወጣው መግለጫ ነው።

 

​"በሱዳን ሰላም ወረደ ማለት ለደቡብ ሱዳንም ሰላም ነው፤ የደቡብ ሱዳን ሰላም እንዲሁ ለሱዳን ሰላም ነው" ሲሉ ሳልቫ ኪር ተናግረዋል።

ዋና ዋና ነጥቦች፦

የቀደመው ስምምነት፦ ጁባ እ.ኤ.አ በጥቅምት 2020 በካርቱም መንግሥት እና በአማፂ ቡድኖች መካከል የሰላም ስምምነት እንዲደረስ አሸማግላለች። ሆኖም በሱዳን ጦር እና በወታደራዊው የፈጥኖ ደራሹ ኃይል መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት ምክንያት የስምምነቱ ትግበራ ተስተጓጉሏል።

ቀጣይ እርምጃዎች፦ የሱዳን ልዑክ እ.ኤ.አ የ2020ውን ስምምነት ለመከለስ እንዲሁም የመሬት ክርክሮችን፣ የዜጎችን መፈናቀል እና በፈጥኖ ደራሹ ኃይሎች የተፈፀሙ ጥሰቶችን ጨምሮ ያልተፈቱ ጉዳዮችን ለመገምገም በቅርቡ ወደ ጁባ እንደሚጓዝ ሚናዊ አረጋግጠዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0