ኢትዮጵያ ለኮንፈረንስ ቱሪዝም ትልቅ ትኩረት ሰጥታ እየሠራች ነው - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን
18:53 18.08.2026 (የተሻሻለ: 19:04 18.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ለኮንፈረንስ ቱሪዝም ትልቅ ትኩረት ሰጥታ እየሠራች ነው - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን
ኢትዮጵያ 76ኛውን የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና የጤና ሚንስትሮች ኮሚቴ ስብሰባ ልታስተናግድ ነው።
ስብሰባው ከነሐሴ 17 እስከ 21 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
ኢትዮጵያ በ2017 ዓ.ም ከ150 በላይ፤ በ2018 ዓ.ም ደግሞ ከ250 በላይ ዓለም ዓቀፍ ጉባኤዎችን እና ስብሰባዎችን አስተናግዳለች።
“ኮንፈረንስ ቱሪዝም እንደ አንድ ትልቅ የኢኮኖሚ ሴክተር ተወስዶ በትኩረት እየተሠራበት ነው” ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር ደኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ ስብሰባውን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል።
የተለያዩ ሀገራት የጤና ሚኒስትሮች እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ኃላፊዎችን ጨምሮ ከ600 በላይ ሰዎች በ76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና የጤና ሚኒስትሮች ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ እንደሚከትሙ የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X