ደቡብ አፍሪካ ንግድ ለእጅ መጠምዘዣነት መዋሉን ትቃወማለች፤ ለፍትሐዊ ዓለም አቀፍ አጋርነትም ትሟገታለች - የፕሬዚዳንቱ ቃል አቀባይ

ሰብስክራይብ
ደቡብ አፍሪካ ንግድ ለእጅ መጠምዘዣነት መዋሉን ትቃወማለች፤ ለፍትሐዊ ዓለም አቀፍ አጋርነትም ትሟገታለች - የፕሬዚዳንቱ ቃል አቀባይ

የደቡብ አፍሪካ ልማት ማኅበረሰብ (ሳድክ)፤ የተናጠል የቅጣት ቀረጦችን አጥብቆ ውድቅ እንዳደረገ እና አነስተኛ ኢኮኖሚዎችን የሚደግፉ፣ በእኩልና ብዝበዛ አልባ አሠራር የሚመራ ዓለም አቀፍ የንግድ ስርዓት እንዲኖር ጥሪ አቅርቧል ሲሉ የፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ቃል አቀባይ ቪንሰንት ማግዌንያ ከ46ኛው ከሳድክ መደበኛ ጉባኤ ጎንዮሽ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ማግዌንያ ያነሷቸው ሌሎች አንኳር ነጥቦች፡-

ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴ፦ አኅጉሪቱ ደቡብ አፍሪካ የቡድን 20 ጉባኤን ካስተናገደች በኋላ ዓለም አቀፍ ትኩረት እያገኘ የመጣውን ማዕድናትን በሀገር ውስጥ የማቀነባበር ሥራ ቅድሚያ ሰጥታ ኢንዱስትሪዋን ማፋጠን አለባት።

መሠረተ ልማት እና ኢነርጂ፦ የክልሉን የኃይል እና የመሠረተ ልማት ክፍተቶች ማሟላት ውህደትን ለማራመድ እና ኢንዱስትሪን ለማሳደግ ወሳኝ ነው።

የክልል ልማት፦ ደቡብ አፍሪካ በሳድክ ሊቀመንበርነቷ፤ የአየር ንብረትና የጂኦፖለቲካዊ ቀውሶችን መቋቋም የሚችሉ ክልላዊ ሥራዓቶችን በመዘርጋት የሕዝቦችን ህይወት ለማሻሻል ትሠራለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0