የመንግሥት ግዢና ንብረት ባለሥልጣን ኬሚካሎችና መድኃኒቶችን ጨምሮ አደገኛ ቁሳቁሶችን ያለ ቅድመ ፈቃድ ማንቀሳቀስ አገደ

© telegram sputnik_ethiopiaየመንግሥት ግዢና ንብረት ባለሥልጣን ኬሚካሎችና መድኃኒቶችን ጨምሮ አደገኛ ቁሳቁሶችን ያለ ቅድመ ፈቃድ ማንቀሳቀስ አገደ
የመንግሥት ግዢና ንብረት ባለሥልጣን ኬሚካሎችና መድኃኒቶችን ጨምሮ አደገኛ ቁሳቁሶችን ያለ ቅድመ ፈቃድ ማንቀሳቀስ አገደ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 18.08.2026
ሰብስክራይብ

የመንግሥት ግዢና ንብረት ባለሥልጣን ኬሚካሎችና መድኃኒቶችን ጨምሮ አደገኛ ቁሳቁሶችን ያለ ቅድመ ፈቃድ ማንቀሳቀስ አገደ

ባለሥልጣኑ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያለፋቸው ኬሚካሎች፣ መድኃኒቶችና ኤሌክትሮኒክሶች መጠን እየጨመረ በመሆኑ በጥንቃቄ እንዲያዙ፣ እንዲመዘገቡና እንዲወገዱ አሳስቧል።

​ቆሻሻዎቹን የሚያጓጉዙ ድርጅቶች የመንግሥት ፈቃድ ማግኘትና ተሽከርካሪዎቻቸውን በጂፒኤስ መከታተል እንደሚኖርባቸውም የግል መገናኛ ብዙኃን የባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱን ኃላፊ ጠቅሶ ዘግቧል።

ባለሥልጣኑ አዲስ ባወጣው አሠራር ካስቀመጣቸው የተወሰኑት መመሪያዎች፦

▪ ተቋማት ኃላፊ ባለሙያ መመደብና በየሦስት ወሩ ሪፖርት ማድረግ ግዴታ አለባቸው፣

▪ የኬሚካል በርሜሎችን ለቤት ውስጥ ውሃ መያዣነት መጠቀም ተከልክሏል፣

▪ ፍሳሾች ወደ አካባቢ ከመለቀቃቸው በፊት መርዛማነታቸው መቀነስ አለበት።

መመሪያው የአደገኛ ቆሻሻዎች አወጋገድን በተመለከት ወጥ አሠራር ባለመኖሩ የነበረውን የአካባቢ ብክለት፣ የእሳትና የኬሚካል ፍሳሽ አደጋ ለመግታት ታስቦ የተዘጋጀ ነው ተብሏል።

 

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0