የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ በደቡብ አፍሪካ ልማት ማኅበረሰብ የሚዲያ ሽልማት በሬዲዮ ጋዜጠኝነት ዘርፍ ሁለተኛ ወጣ
19:15 17.08.2026 (የተሻሻለ: 19:24 17.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የስፑትኒክ አፍሪካ ዘጋቢ በደቡብ አፍሪካ ልማት ማኅበረሰብ የሚዲያ ሽልማት በሬዲዮ ጋዜጠኝነት ዘርፍ ሁለተኛ ወጣ
የሲያክጋ ጥላዲ "የደቡባ አፍሪካ ልማት ማኅበረሰብ አንድነት እና ማዕቀቦች በዚምቧቤ" የተሰኘው አሸናፊ ሥራ፤ ማዕቀቦች በዚምቧቤ ላይ ያሳደሩትን ተፅዕኖ እና የሀገሪቱን የመቋቋም አቅም የዳሰሰ ሲሆን ከሌሶቶ፣ ናሚቢያ እና ዚምቧቤ የተሳተፉ ባለሥልጣናት ማዕቀቡ እንዲነሳ ያቀረቡትን ሙግት እና የቀጣናዊ ትስስርን አስፈላጊነት ያጎሉበትን ሁኔታ አካቷል።
ሽልማቱ ይፋ የተደረገው በደርባን በተካሄደው 46ኛው የደቡብ አፍሪካ ልማት ማኅበረሰብ የመሪዎች ጉባኤ ወቅት ነው።
ውድድሩ በደቡብ አፍሪካ ልማት ማኅበረሰብ አባል ሀገራት መካከል ስለ ቀጣናዊ ትስስር እና ትብብር የጎላ ግንዛቤ ለሚፈጥሩ የጋዜጠኝነት ሥራዎች ዕውቅና ይሰጣል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X