የጤና ሚኒስቴር በፎርሙላ ወተት አጠቃቀም እና ስርጭት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ሊያደርግ ነው
18:42 17.08.2026 (የተሻሻለ: 18:44 17.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የጤና ሚኒስቴር በፎርሙላ ወተት አጠቃቀም እና ስርጭት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ሊያደርግ ነው
በህጻናት ፎርሙላ ወተት አጠቃቀም፣ ስርጭት እና ማስታወቂያዎች ላይ የሚደረገው ቁጥጥር እና ክትትል ከዚህ ቀደሙ የበለጠ ጥብቅ ሆኖ እንደሚተገበር ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
መነሻ ምክንያቶች፦
ምርቶቹ ከውጭ የሚገቡ በመሆኑ በቤተሰብ እና በሀገር ደረጃ ከፍተኛ የወጪ ጫና ማሳደራቸው፣
ያለአግባብ ፎርሙላ ወተት የሚወስዱ ህጻናት ለተለያዩ የጤና እክሎች እና ለተጨማሪ የሕክምና ወጪ መጋለጣቸው፣
እናቶች የተፈጥሮ ጡት ማጥባትን እንዲተው የሚያደፋፍሩ የተጋነኑ የማስታወቂያ ዘመቻዎችን መግታት አስፈላጊ በመሆኑ።
እርምጃዎች፦
◻ የፎርሙላ ወተት ስርጭትና አጠቃቀም በህጻናት ምግብ ቁጥጥር መመሪያ መሠረት በትክክል በሚያስፈልግባቸው አጋጣሚዎች ብቻ እንዲውል ይደረጋል።
◻ የሕግ ማዕቀፎችን በመጣስ የሚደረጉ የስርጭትና የማስታወቂያ እንቅስቃሴዎች ላይ ጥብቅ ክትትል ይደረጋል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X