በአዲስ አበባ ከተማ በአውቶቡስ ለመጓዝ የወረቀት ትኬት መቁረጥ ሙሉ በሙሉ ሊቀር ነው
16:04 17.08.2026 (የተሻሻለ: 16:14 17.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በአዲስ አበባ ከተማ በአውቶቡስ ለመጓዝ የወረቀት ትኬት መቁረጥ ሙሉ በሙሉ ሊቀር ነው
የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት በ2019 ዓ.ም. የወረቀት ትኬትን ሙሉ በሙሉ በማስቀረት ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ክፍያ ብቻ አገልግሎቱ እንደሚሰጥ ማስታወቁን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ቁልፍ መረጃዎች፦
ተሳፋሪዎች በሚዘጋጅ ካርድ ወይም በሞባይል መተግበሪያ አማካኝነት በቀላሉ ክፍያ መፈጸም ይችላሉ።
እንደ ፍላጎትና አቅም ከ1 ሳምንት እስከ 1 ዓመት የሚያገለግል የመጓጓዣ ትኬት አስቀድሞ መቁረጥ ይቻላል።
ቴክኖሎጂውን በቀላሉ መጠቀም ለማይችሉ ነዋሪዎች ምቹ የሆነ ተንቀሳቃሽ የትኬት መቁረጫ አማራጭ ይዘጋጃል።
አዲሱ አሠራር ተገልጋዮች በየፌርማታው የሚያጋጥማቸውን ረጅም ሰልፍና እንግልት በማስቀረት የከተማዋን የትራንስፖርት አገልግሎት የተቀናጀና ፈጣን እንደሚያደርገው ታምኖበታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X