ከ10 የመስኖ ፕሮጀክቶች 9ኙ ተጠናቀዋል - የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር

ሰብስክራይብ

ከ10 የመስኖ ፕሮጀክቶች 9ኙ ተጠናቀዋል - የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር

ሚኒስቴሩ ባለፉት ሁለት የበጀት ዓመታት በዕቅድ ከያዛቸው የመስኖ ፕሮጀክቶች 90% የሚሆኑትን ማጠናቀቁንና መሬት የማልማት አጠቃላይ አቅም ወደ 200 ሺህ ሄክታር ገደማ መድረሱን አስታውቋል።

ዋና ዋና መረጃዎች፦

▪ የወልመል፣ የጎዴ እና የቄጦ የመስኖ ግድቦች ግንባታ የተጠናቀቀ ሲሆን ላለፉት 15 ዓመታት ዘግይተው የነበሩት የአርጆ እና የመገጭ ፕሮጀክቶችም አሁን ወደ ማጠናቀቂያው ምዕራፍ ደርሰዋል።

▪ ፕሮጀክቶቹ ቀደም ሲል ይስተዋሉ የነበሩ የሀብት ብክነትና የፕሮጀክቶች መጓተት ችግሮችን በቀረፉ 25 አዳዲስ የጥራትና የግንባታ መስፈርቶች መሠረት የተከናወኑ ናቸው።

▪ለቀጣዮቹ 15 ዓመታት የሚያገለግል ብሔራዊ የመስኖ መሪ ፍኖተ ካርታ እየተዘጋጀ የሚገኝ ሲሆን በ2019 የበጀት ዓመት ደግሞ የወይቦ ግድብን ጨምሮ አዳዲስ ፕሮጀክቶች ይጀመራሉ።

በአፋር፣ አሮሚያ እና ሲዳማ ክልሎች የተገነቡ የከሰም፣ ቄጦ እና ጊዳቦ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0