የሶማሊያ አዲሱ የፓርላማ አፈ ጉባኤ በመንግሥትና በተቃዋሚዎች መካከል ያለውን ውጥረት ያረግቡታል?

የሶማሊያ አዲሱ የፓርላማ አፈ ጉባኤ በመንግሥትና በተቃዋሚዎች መካከል ያለውን ውጥረት ያረግቡታል?
አብዱልቃድር ሞሐመድ ኑር ጃማ የሶማሊያ አዲስ የፓርላማ አፈ ጉባኤ ሆነው መመረጣቸው የፖለቲካ ውጥረቱን ለማርገብ ይረዳል የሚል ተስፋን ያጫረ ቢሆንም፤ ተንታኞች ግን ውጤታማነታቸው ከተቃዋሚዎች ጋር በሚኖራቸው አቀራረብ ላይ የተመሰረተ ነው ይላሉ።
የተንታኞች ዋና ዋና እይታዎች፦
🟠 ጃማ ከአገር ውስጥ የፖለቲካ ኃይሎች እና ከዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ጥብቅ ግንኙነት የገነቡ በመሆናቸው የአገሪቱን አቅጣጫ በመምራት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዲጫወቱ ያስችላቸዋል ሲሉ የሞቃዲሾ ጥናት ማዕከል መሪ አብዲራህማን ኢብራሂም አብዲ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
🟠 በመንግሥትና በተቃዋሚዎች መካከል ያለው ግጭት መሠረቱ የፖለቲካና የሕገ-መንግሥት ጉዳዮች እንጂ የቴክኒክ ጉዳይ አይደለም ያሉት ተንታኙ ኦማር ሞሐመድ፤ ጃማ የነበረውን ልዩነት ለማጥበብ የሚያስችል ሁሉንም ያካተተ አቀራረብ ካልተከተሉ በቀር የእሳቸው መመረጥ ብቻውን የተቃዋሚዎችን አቋም አይለውጠውም ሲሉ አክለዋል።
ጃማ ነሐሴ 2 የሶማሊያ ፓርላማ አፈ ጉባኤ ሆነው የተመረጡ ሲሆን፤ ተፎካካሪያቸው ካገኙት 38 ድምፅ አንፃር ከፍተኛ የሚባል የ134 ድጋፍ ድምፅ አግኝተዋል። የቀደሙት አፈ ጉባኤ የአገልግሎት ዘመን በሰኔ ወር ከተጠናቀቀ በኋላ ቦታው ያለ ተተኪ ክፍት ሆኖ ቆይቶ ነበር።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X