- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

የሳህል ሀገራት አዲስ ስትራቴጂ፡ የ2032 አፍሪካ ዋንጫን የማስተናገድ ጥያቄ እና የቀጣናው አዲሱ የትብብር ምዕራፍ

የሳህል ሀገራት አዲስ ስትራቴጂ፡ የ2032 አፍሪካ ዋንጫን የማስተናገድ ጥያቄ እና የቀጣናው አዲሱ የትብብር ምዕራፍ
ሰብስክራይብ

" በሁሉም መስፈርቶች—በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እና በጂኦ-ስትራቴጂ—ይህ የጨረታ ጥያቄ ታላቅ የዲፕሎማሲ ስኬት ነው። ውድድሩን ማስተናገድ የታገደ/የተገለለ የሚለውን አስተሳሰብ ሙሉ በሙሉ ያስቀራል፣ ያከሽፋልም። [...] እስካሁን ተጽእኖ ፈጥሮ የቆየው የታሪክ አቀራረብ ይህንን ቀጠና በግጭት ብቻ አሳንሶ አሳይቶታል። ይህ የአፍሪካ ዋንጫን የማዘጋጀት ጥያቄ የምድር ላይ እውነታውን ያጋልጣል—ቀጠናው ለዓለም አቀፍ አጋርነት ክፍት እና ብቁ መሆኑን ያሳያል፡፡" ሲሉ የፓን-አፍሪካኒዝም እና የልማት ስፔሻሊስት ኦሉሶጂ አጃኦ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፖድካስት፤ በመጀመሪያው ክፍል የሳህል ሀገራት ህብረት የተጣለባቸውን የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ጫናዎች በመቃወም፣ ዲፕሎማሲያዊ ተጽዕኖአቸውን ለማሳደግ እና ቀጣናዊ መሰረተ-ልማቶችን ለማፋጠን ያቀረቡትን የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎችን በ2032 በጋራ የማስተናገድ ጥያቄ እና የስፖርት ዲፕሎማሲ ፋይዳን ከፓን-አፍሪካኒስት እና የልማት ስፔሻሊስቱ ኦሉሶጂ አጃኦ ጋር በጥልቀት እንወያያለን። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ፤ የኢትዮጵያን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤን ማዕከል በማድረግ፣ ከውጭ የሚገቡ የህግ ማዕቀፎች ያሉባቸውን ጉድለቶች በመዳሰስ እና እንደ ሽምግልና እና ገዳ ያሉ ባህላዊ የእርቅ መድረኮችን በማዘመን ዘላቂ ሰላምን እና ሀገራዊ ሉዓላዊነትን የመገንባት ሂደትን ከህግ እና የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም ጋር ሰፊ ውይይት አድርገናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ይከታተሉ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0