በምስራቅ ኮንጎ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማፋጠን ታንዛኒያ እና ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የንግድ ኮሪደር መስርተዋል - ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopiaበምስራቅ ኮንጎ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማፋጠን ታንዛኒያ እና ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የንግድ ኮሪደር መስርተዋል - ባለሙያ
በምስራቅ ኮንጎ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማፋጠን ታንዛኒያ እና ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የንግድ ኮሪደር መስርተዋል - ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 12.08.2026
ሰብስክራይብ

በምስራቅ ኮንጎ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማፋጠን ታንዛኒያ እና ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የንግድ ኮሪደር መስርተዋል - ባለሙያ

ሁለቱ ሀገራት፣ የኮንጎ የትራንስፖርት መሠረተ ልማት ወደ ታንዛኒያ ያለውን ተደራሽነት ለማሻሻል፤ የኮንጎን ማኔማ ክልል ከምስራቅ አፍሪካ ለማገናኘት አዲስ የንግድ ኮሪደር አስጀምረዋል፡፡

የባሕር በር አላባዋ ማኔማ በወርቅና በኮልታኔ የበለፀገች ብትሆንም ወደ ውቅያኖስ ወደብ እና ለመሠረታዊ ሸቀጦች ያላት ተደራሽነት ዉሱን መሆኑንየኮኖጎ የኢኮኖሚ ጉዳዮች ተንታኝ አሳኒ ኪዙንጉሩካ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ታንዛኒያ ለምስራቃዊ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ወሳኝ የንግድ መግብያ ልትሆን ትችላለች፤ ይህም በመላው ምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ሰፊ የንግድ ዕድሎችን እንደሚከፍት ባለሙያው ገልፀዋል።

እንደ ባለሙያው  ሐሳብ የሀገራቱ አዲሱ ትብብር ዋና ዋና መሠረቶች:-

🟠ሎጀስቲክስ እና አቅርቦት:- የውቅያኖስ ወደብ ተደትራሽነት እና እንደ ነዳጅና ስኳር ያሉ አስፈላጊ ምርቶችን ማቅረብ።

🟠የማዕድን ዘርፍ ዕድገት:- የማኔማን ሰፊ የማዕድን ሀብት ለክልላዊ ገበያዎች እንዲውል ማስቻል።

🟠የፋይናንስ ውህደት:- የታንዛኒያ ንግድ ባንክ በንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ያለውን ተሳትፎ ማስፋት።

🟠መሠረተ ልማት:- ዋና ቀጣናዊ የባቡር መስመር ትስስርን ማሳደግ።

"በርግጥም ትብብሩ በጣም ትርጉም ያለው ይሆናል፤ በመላው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ሀገራት ያሉትን ህዝቦች ይበልጥ ማቀራረቡን እንቀጥላለን" ሲሉ ኪዙንጉሩካ አጽንዖት ሰጥተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

 ስፑትኒክ ኢትዮጵያ |  መተግበሪያ |  X

አዳዲስ ዜናዎች
0