ዓለም አቀፉ የምግብ ስርዓት "ሱፐር ኤል ኒኖን" ለመቋቋም የተሻለ ዝግጅት አለው - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኤጀንሲ
ዓለም አቀፉ የምግብ ስርዓት "ሱፐር ኤል ኒኖን" ለመቋቋም የተሻለ ዝግጅት አለው - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኤጀንሲ
በሰብል ሳይንስ ዘርፍ የተደረጉ መሻሻሎች፣ የምግብ እህል ክምችት በከፍተኛ ደረጃ መጨመር እና የአዳዲስ ላኪ ሀገራት መበራከት የዓለም አቀፉን የምግብ ስርዓት በማጠናከር መጪውን "ሱፐር ኤል ኖ" ለመቋቋም ያስችላሉ ሲል የተመድ የምግብ እና የእርሻ ድርጅት (ፋኦ) ገልጿል።
ዋና ዋና ምክንያቶች፦
ዘመናዊ መስኖ፣ ድርቅን የሚቋቋሙ የእህል ዝርያዎች እና በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የሚሠሩ የእርሻ ምክር መስጫ ዘዴዎች አርሶ አደሮች በድርቅ ወቅት እንኳ ምርታማነታቸውን እንዲጠብቁ አግዘዋል።
በተለይም በሕንድ እና ቻይና የታየው የሩዝና የስንዴ ሰብል ከፍተኛ ክምችት ሊከሰቱ የሚችሉ የምግብ እጥረት ስጋቶችን ለመቀነስ እንደ መከላከያ ያገለግላሉ።
እንደ ብራዚል እና ሩሲያ ያሉ አዳዲስ እህል ላኪ ሀገራት እ.ኤ.አ በ1997-98 እና በ2015-16 ከተከሰቱት ከባድ የኤል ኒኖ ክስተቶች ወዲህ ለዓለም አቀፉ ገበያ የሚያቀርቡትን የምግብ መጠን በከፍተኛው ጨምረዋል።
የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት የነዳጅ እና የማዳበሪያ አቅርቦት ላይ እንቅፋት ቢፈጥርም፤ ባለሙያዎች ግን የዓለም የምግብ ስርዓት ከቀደሙት ቀውሶች ይልቅ የአሁኑን ተፅዕኖ ለመቋቋም የተሻለ ዝግጅት እንዳለው እየተናገሩ ይገኛሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X