ኒያሜ የሳኀል ቀጣናን ደህንነት እና መረጋጋት ለማጠናከር ያለመ ክልላዊ የወጣቶች መድረክ አስተናገደች
18:26 11.08.2026 (የተሻሻለ: 18:34 11.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኒያሜ የሳኀል ቀጣናን ደህንነት እና መረጋጋት ለማጠናከር ያለመ ክልላዊ የወጣቶች መድረክ አስተናገደች
ከ10 ሀገራት የተውጣጡ 2 ሺህ 500 ወጣቶች በፈጠራ፣ ሥራ ፈጠራ እና የዕውቀት ልውውጥ ዙሪያ ለሦስት ቀናት ኒጀር ውስጥ ተሰብስበው መክረዋል። ስፑትኒክ አፍሪካ በሳኀል ወጣቶች ላይ የተደቀኑ ዋና ዋና ፈተናዎችን ለመረዳት ከተሳታፊዎች እና ባለሙያዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጓል።
ዋናው ፈተና ሥራ አጥነት ነው፦
በተለይም "ወጣቶች ከ60% በላይ የሚሆነውን የአፍሪካ ሕዝብ ቁጥር በሚሸፍኑበት ሁኔታ፤ በሳኀል ቀጣና ደህንነትን ማረጋገጥ እና ሥራ አጥነትን መቀነስ አስፈላጊ ጉዳዮች ናቸው" ሲሉ የቻድ የወጣቶች እና የመዝናኛ ዋና ዳይሬክተር ሀሳን ሚሄዲ አህማት ገልጸዋል።
ወጣቶች የሚያስፈልጋቸው ነገር ምንድነው? ወጣቶች ስኬታማ ለመሆን እውነተኛ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል። የኒያሜ ቀጣናዊ የወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሱማና ሰይኒ አብዱል ወሃብ፤ "አንድ ወጣት ሥራ ማስጀመሪያ ገንዘብ ሳያመቻችለት የሀገሩን ኢኮኖሚ እንዲገነባ መጠየቅ አይቻልም" ብለዋል።
ለነዚህ ተግዳሮቶች ተገቢውን ምላሽ መስጠት፤ "የበለጸገች ዓለም እንዲሁም ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች ኢኮኖሚውን የሚመሩበት እና ሀገራቸውን የሚለውጡበት ሳኀልን ለመፍጠር ያግዛል" ሲሉ የዩኤንዲፒ ተወካይ ካሊድ ረሃማኔ ንዳዬ አጠቃልለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X