የቻድ ፕሬዚዳንት በነጻነት ቀን ዋዜማ ለሀገር ወዳድነትና አንድነት ጥሪ አቀረቡ

ሰብስክራይብ

የቻድ ፕሬዚዳንት በነጻነት ቀን ዋዜማ ለሀገር ወዳድነትና አንድነት ጥሪ አቀረቡ

ማሃማት ዴቢ ኢትኖ ቻድ 66ኛውን የነጻነት በዓሏን ለማክበር በመዘጋጀት ላይ በምትገኝበት ወቅት ለሀገሪቱ ዜጎች ባደረጉት ንግግር "በውጭ ተፅዕኖ ስር" የሆኑ ቻዳውያን ሀገር ወዳድነትና አንድነትን እንዲቀበሉ አሳስበዋል።

ፕሬዚዳንቱ "በመለያየት ወደፊት የሚራመድ ሀገር የለም" ያሉ ሲሆን የሕዝቦች ግጭት ልማት የሚያደናቅፍ መሆኑን በመጥቀስ ለሰላም፣ ሥርዓት እና ብሔራዊ አንድነት ጥሪ አቅርበዋል።

 

ማሃማት ዴቢ ኢትኖ በንግግራቸው ይፋ ያደረጓቸው ጉዳዮች፦

ለበርካታ ታራሚዎች የፕሬዝዳንታዊ ምኅረት፣

ዝቅተኛ አፈፃፀም ባሳዩ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎች፣

በሙስና እና በሀብት ምዝበራ ላይ የሚወሰዱ ጥብቅ እርምጃዎች፣

የመከላከያ እና የደህንነት ኃይሎችን ማጠናከር እና ማዘመን፣

አገልግሎትን ወደ ታችኛው የሥልጣን እርከን በፍጥነት ማከፋፈል፣

ለውሃ፣ ኤሌክትሪክ፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ጤና እና ትምህርት ቅድሚያ መስጠት።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0