ማላዊ 10 ሜጋዋት የሚያመነጭ የፀሐይ ኃይል ፋብሪካ ከፈተች

ሰብስክራይብ

ማላዊ 10 ሜጋዋት የሚያመነጭ የፀሐይ ኃይል ፋብሪካ ከፈተች

ፋብሪካው የሀገሪቱን የኃይል አማራጮች የማስፋፋት ዕቅድ አካል ነው። 12 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ተደርጎበት በአሁኑ ወቅት ወደ ሀገሪቱ ብሔራዊ የኤሌክትሪክ መስመር ኃይል ማሰራጨት ጀምሯል። የ50 ሜጋዋት ፕሮጀክት የመጀመሪያው ምዕራፍ ሲሆን በቀጣይም ተጨማሪ አቅም እንደሚገነባበት ይጠበቃል።

ማመንጫውን የተመለከቱ ቁልፍ ነጥቦች፦

የኢነርጂ ሚኒስትር ጂን ማታንጋ የማዕከሉ የሙከራ ሂደት በስኬት መጠናቀቁን ያረጋገጡ ሲሆን ይህም የማላዊን የኃይል አማራጮች ለማስፋፋትና በውኃ ኃይል ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ ቁልፍ እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል።

መንግሥት 538 ሜጋዋት የሚያመነጨውን ትልቁን የመፓታማንጋ የውኃ ኃይል ፕሮጀክት እውን ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን ሙሉ ግንባታው እ.ኤ.አ በ2027 ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል። በተጨማሪም ከሞዛምቢክ ጋር በሚደረግ አዲስ የኤሌክትሪክ መስመር ግንባታ ተጨማሪ ኃይል ይገኛል ተብሏል።

የማላዊ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዊሊያም ሊያቡንያ፤ የሳሊማ ፕሮጀክት ሁለተኛ ምዕራፍ የአዋጭነት ጥናት እየተካሄደ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0