በማራኬሽ በቱሪዝም ስም በእንስሳት ላይ የሚፈጸም ብዝበዛ እንዲቆም ተጠየቀ

ሰብስክራይብ

በማራኬሽ በቱሪዝም ስም በእንስሳት ላይ የሚፈጸም ብዝበዛ እንዲቆም ተጠየቀ

በሞሮኮ ማራኬሽ ከተማ እባቦችን፣ የባርበሪ ዝንጀሮዎችን እና የፈረስ ሠረገላዎችን ለቱሪስት መስህብነት መጠቀም እንዲቆም የሚጠይቅ ዘመቻ በ "ማይፒቲሽን" ድረ-ገፅ ላይ ከ17 ሺህ በላይ ፊርማዎችን አሰባስቦ ለከተማዋ ማዘጋጃ ቤት እና ለአካባቢው ባለሥልጣናት አቅርቧል።

የአቤቱታው ዋና ዋና ዝርዝሮች፦

◻ እንስሳቱ ለከባድ እንግልት የተጋለጡ ናቸው የሚለው አቤቱታው፤ እባቦች ያለ ጥላና ውሃ እንደሚቀመጡ፣ ዝንጀሮዎች ለሰዓታት በሰንሰለት ታስረው እንደሚቆዩ እንዲሁም የሠረገላ ፈረሶች በድካምና በጉዳት ላይ ሆነው እንዲሠሩ እንደሚገደዱ ያትታል።

◻ አቤቱታው በጀማ ኤል-ፍና አደባባይ እባቦችና ዝንጀሮዎችን ለሕዝብ ማሳየት እንዲቆም፣ እንስሳቱ ከብዝበዛ እንዲወጡ እና በሠረገላ ፈረሶች ላይ የግዴታ የእንስሳት ሕክምና ምርመራ ተደርጎ እንስሳቱን በሚያሰቃዩ ባለቤቶች ላይ ቅጣት እንዲጣል ይጠይቃል።

◻ አቤቱታ አቅራቢዎች ባሕላዊ ቅርስ ለእንስሳት ስቃይ ምክንያት ሊሆን ሊአይገባም ሲሉ ይሞግታሉ። ማራኬሽ የእንስሳትን ስቃይ የቱሪዝም ልምድ አካል ሳታደርግ የሕዝብ ቦታዎቿን እንድትንከባከብም አጥብቀው ጠይቀዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0