በናይጄሪያ በላሳ ትኩሳት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 237 ደረሰ፤ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከአንድ ሺህ በላይ ማለፉን የጤና ባለሥልጣናት ገለጹ
15:50 11.08.2026 (የተሻሻለ: 15:54 11.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በናይጄሪያ በላሳ ትኩሳት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 237 ደረሰ፤ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከአንድ ሺህ በላይ ማለፉን የጤና ባለሥልጣናት ገለጹ
ላሳ ትኩሳት በዋነኝነት በአይጦች በተበከለ ምግብ ወይም በበሽታው ከተያዘ ሰው የሰውነት ፈሳሽ ጋር በሚደረግ ቀጥተኛ ንክኪ የሚተላለፍ ከባድ የደም መፍሰስ በሽታ ነው።
በሐምሌ ወር የበሽታው የሞት ምጣኔ እ.ኤ.አ በ2025 ከነበረበት 18.8% ወደ 23.7% ከፍ እንዳለ የናይጄሪያ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል አስታውቋል።
ማዕከሉ ለሞት ምጣኔ ጭማሬው የሚከተሉትን ምክንያቶች ጠቅሷል፦
የዘገየ የህክምና አገልግሎት፣
የንጽህና አጠባበቅ ጉድለት፣
ዝቅተኛ የማኅበረሰብ ግንዛቤ።
ቫይረሱ በ23 ግዛቶች በሚገኙ 116 የአካባቢ አስተዳደር ቦታዎች የተሰራጨ ሲሆን በዋነኝነት እድሜያቸው ከ21 እስከ 30 ዓመት የሆኑ ሰዎችን እንደሚያጠቃ ማዕከሉ አመልክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X