ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ድርድር ላይ የሩሲያ ሚና እንዲኖር ድጋፏን ሰጠች
19:20 10.08.2026 (የተሻሻለ: 19:24 10.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ድርድር ላይ የሩሲያ ሚና እንዲኖር ድጋፏን ሰጠች
ኢራን በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ በኩል የሚደረግ ደህንነቱ የተጠበቀ የባሕር ጉዞን ሁልጊዜም እንደምትደግፍ፤ ሆኖም መተላለፊያው ለንግድ መርከቦች ትራንስፖርት እንጂ ለወታደራዊ አላማዎች ሊውል እንደማይገባው፤ ለኢራን የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃሚድ ጋንባሪ አስታውቀዋል።
የወሽመጡን ደህንነት ለማረጋገጥ በሁሉም ባለድርሻ አካላት ማለትም በባሕር ዳርቻ ሀገራት፣ በሆርሙዝ መስመር የኃይል አቅርቦት ላይ ጥገኛ በሆኑ ሀገራት እና መስመሩን በሚጠቀሙ የኢነርጂ ምርት ላኪዎች መካከል "በመከባበር ላይ የተመሠረተ ውጤታማ ውይይት" እንደሚያስፈልግ ጋንባሪ ገልጸዋል።
"ሩሲያ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባል እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ድምጿ የሚሰማ ኃይል እንደመሆኗ መጠን ከፍተኛ ሚና መጫወት ትችላለች" ያሉት ጋንባሪ፤ አክለውም "የሩሲያ ሚና በጉዳዩ ዙሪያ ተሳታፊ በሆኑ ወገኖች መካከል በመከባበር ላይ የተመሠረተ ውይይት እንዲደረግ መንገድ ሊከፍት ይችላል" ብለዋል።
ኢራን ከታላላቅ ኃያላን ሀገራት ነፃ ሆና የራሷን ብሔራዊ ጥቅም ማስከበሯን ትቀጥላለች ሲሉም አስረግጠዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X