ሩሲያ ዩክሬን ሲቪሎች ላይ የፈጸመችውን የሽብር ጥቃት ኮነነች

© telegram sputnik_ethiopiaሩሲያ ዩክሬን ሲቪሎች ላይ የፈጸመችውን የሽብር ጥቃት ኮነነች
ሩሲያ ዩክሬን ሲቪሎች ላይ የፈጸመችውን የሽብር ጥቃት ኮነነች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.08.2026
ሰብስክራይብ

ሩሲያ ዩክሬን ሲቪሎች ላይ የፈጸመችውን የሽብር ጥቃት ኮነነች

 

"የኪየቭ አገዛዝ በተለያዩ የሩሲያ ክልሎች በሚገኙ ሲቪሎች ላይ በየዕለቱ የሚፈጽመውን አረመኔያዊ ድርጊት በመቀጠል፤ ሕፃናት፣ ሴቶችና አረጋውያንን ጨምሮ በሰዎች ሕይወትና አካል ላይ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል" ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ገልጸዋል።

ቃል አቀባይዋ ይህንን ያሉት እሑድ እና ሰኞ በቤልጎሮድ እና ኒዥኔካምስክ በሚገኙ የሲቪል ተቋማት ላይ የተፈጸሙትንና ታዳጊዎችን ጨምሮ በደርዘን ለሚቆጠሩ መጎዳት ምክንያት የሆኑትን የቅርብ ጊዜ የዩክሬን ድሮን ጥቃቶች በማስመልከት ነው።

ዲፕሎማቷ ያነሷቸው ሌሎች ነጥቦች፦

በጥቃቱ የተሳተፉ አካላት በሙሉ ተለይተው ከባድ ቅጣት ይቀጣሉ።

ሞስኮ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጥቃቶቹን አጥብቀው እንዲኮንኑ ትጠይቃለች።

ሩሲያ የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ዝምታ እንደ ተባባሪነት እና በሩሲያ ሕዝብ ላይ ለሚፈጸም ተጨማሪ ጥቃት እንደተሰጠ ማበረታቻ አድርጋ ትቆጥረዋለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0