ሱዳን የሻይ ገበያዋን ለኬንያ መልሳ ለመክፈት ዝግጁ መሆኗ ተዘገበ

ሰብስክራይብ

ሱዳን የሻይ ገበያዋን ለኬንያ መልሳ ለመክፈት ዝግጁ መሆኗ ተዘገበ

 

"በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ንግድ ለማቀላጠፍ ውይይቱን በከፍተኛ ደረጃ እንገፋበታለን" ሲሉ በኬንያ የሱዳን አምባሳደር ካማል ጃባራ ጉባራ መናገራቸውን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

እርምጃው የቀድሞ የኬንያ ምክትል ፕሬዚዳንት ካሎንዞ ሙስዮካ፤ በናይሮቢ የሚገኘውን የሱዳን ኤምባሲ በመጎብኘት ለሱዳን መንግሥት ያቀረቡትን ይፋዊ ጥሪ ተከተሎ የመጣ ነው።

​ℹ በሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት ሳቢያ እ.ኤ.አ በመጋቢት 2025 የተጣለው እገዳ፤ በኬንያ የሻይ ኢንዱስትሪ ላይ ከባድ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን በየዓመቱ እስከ 70 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ሻይ ይገዛ ከነበረው ገበያ ከ24 ሚሊዮን ዶላር በላይ አሳጥቷል።

 

"እስከዛሬ ድረስ ለሱዳን ገበያ ተብሎ በልዩ ሁኔታ የተቀናበረና ከ10.3 ሚሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያለው ከ3.44 ሚሊዮን ኪ.ግ በላይ የሻይ ቅጠል ምርት በሞምባሳ መጋዘኖች ውስጥ ተከማችቶ ይገኛል" ሲሉ ሙስዮካ በ 'ኤክስ' ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

ይህን የሻይ ምርት በቀላሉ ወደ ሌሎች ገበያዎች ማዞር አለመቻሉ በላኪዎች ላይ ኪሳራ ማድረሱን፣ የጨረታ ዋጋ እንዲወርድ ማድረጉን እና የገበሬዎችን ገቢ መቀነሱም ተገልጿል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0