የሩሲያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በዓለም አትሌቲክስ ላይ ሁለተኛውን ክስ መሠረተ

© telegram sputnik_ethiopiaየሩሲያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በዓለም አትሌቲክስ ላይ ሁለተኛውን ክስ መሠረተ
የሩሲያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በዓለም አትሌቲክስ ላይ ሁለተኛውን ክስ መሠረተ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 10.08.2026
ሰብስክራይብ

የሩሲያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በዓለም አትሌቲክስ ላይ ሁለተኛውን ክስ መሠረተ

የመላው-ሩሲያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በዓለም አትሌቲክስ የተጣለበትን ዕቀባ በመቃወም በስፖርት የግልግል ዳኝነት ፍርድ ቤት አዲስ ክስ መስርቷል።

የመላው-ሩሲያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዋና ዓላማ የሩሲያ አትሌቶች ወደ ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ መድረክ መመለሳቸውን ማረጋገጥ እና ፌዴሬሽኑ ላይ የተጣለውን ዕገዳ ማስነሳት ነው። ፌዴሬሽኑ እገዳዎቹ መብቶቹን የሚጥሱ እና የሩሲያ አትሌቲክስ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሙሉ በሙሉ እንዳይወከል የገደቡ ናቸው በማለት እየተከራከረ ነው።

የሩሲያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዕቀባው ነቃሲ እና ፖለቲካዊነቱ እንዳሳሰበው አጽንዖት ሰጥቷል። በሩሲያ ላይ የተያዘው ጠንካራ አቋም በዋነኝነት እየተራመደ ያለው፤ በወቅቱ የዓለም አትሌቲክስ ኃላፊ እና በቀድሞው የብሪታንያ ወግ አጥባቂ ፓርቲ የፓርላማ አባል ሴባስቲያን ኮ አማካኝነት ብቻ መሆኑን ፌዴሬሽኑ ጠቁሟል። የሴባስቲያን ኮ ውሳኔ መዘዞች የሩሲያን አትሌቲክስ ብቻ ሳይሆን፤ ዓለም አቀፉንም ስፖርት የሚጎዱ እንዲሁም የእኩልነትን እና የገለልተኛነት መርሆችን የሚሸረሽሩ ናቸው ብሏል።

“በመላው-ሩሲያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ላይ የተጣለው ማዕቀብ ታይቶ የማይታወቅ ነው — ሌላ የትኛውም የስፖርት ፌዴሬሽን ላይ እንዲህ ዓይነት ከባድ ገደቦች ተጥለው አያውቁም። እገዳዎቹ የፌዴሬሽኑን በአግባቡ የመሥራት አቅም ከማደናቀፍ ባለፈ፤ በሩሲያ የአትሌቲክስ ዕድገትን የሚገቱ እና በተለይም ወጣት አትሌቶች ስፖርታችንን በዓለም አቀፍ መድረክ በአግባቡ እንዳይወክሉ የሚከለክሉ ናቸው። ለዚህም ነው መብቶቻችንን ያለማቋረጥ የምንከላከለው እና ዕቀባዎቹ በፍርድ ቤቶች እንዲነሱ የምንታገለው፤ ይህንን ሥራችንን እንቀጥላለን። ፍትሕን ለመመለስ ቀጣይ እርምጃችንን እያጤንን እንገኛለን” ሲሉ የፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈፃሚ ቦሪስ ያሪሼቭስኪ አብራርተዋል።

የመላው-ሩሲያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፤ የዓለም አትሌቲክስ የሩሲያ አትሌቶችን በስሩ ከሚካሄዱ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ያገደበትን ውሳኔ ማራዘሙን በመቃወም ያቀረበውን አቤቱታ የስፖርት የግልግል ዳኝነት ፍርድ ቀደም ሲል ተቀብሏል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0