ቡርኪና ፋሶ የነዳጅ አቅርቦትን ለማረጋጋት የናፍጣ ዋጋን በሊትር ከ1.18 ወደ 1.32 ዶላር አሳደገች
16:11 10.08.2026 (የተሻሻለ: 16:14 10.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ቡርኪና ፋሶ የነዳጅ አቅርቦትን ለማረጋጋት የናፍጣ ዋጋን በሊትር ከ1.18 ወደ 1.32 ዶላር አሳደገች
የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆነው ይህ ውሳኔ፤ የነዳጅ አቅርቦትን ለማረጋጋት አስፈላጊ ነው ብለዋል።
የዋጋ ጭማሪው ምክንያቶች፦
1⃣ መንግሥት ነዳጅ ላይ ድጎማ በማድረግ ዋጋን ለማረጋጋት ቢጥርም፤ ወጪው ከሀገሪቱ አቅም በላይ እየሆነ መምጣቱን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። ከፈረንጆቹ 2026 መግቢያ ጀምሮ እስካሁን ለድጎማ ከ105 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ የተደረገ ሲሆን እርምጃ ካልተወሰደ ይህ ቁጥር ከ238 ሚሊዮን ዶላር በላይ ሊያልፍ እንደሚችል ተገልጿል።
2⃣ የናፍጣ ዋጋ ውድ ከሆነባቸው ጎረቤት ሀገራት በርካታ ተሽከርካሪዎች ወደ ቡርኪና ፋሶ በመግባት ነዳጅ ይሞላሉ። አጓጓዦቹ ተጨማሪ ነዳጅ በበርሜል ጭነው የሚወጡ በመሆኑ፤ ለሀገሪቱ የነዳጅ እጥረትና አላስፈላጊ ፍጆታ ምክንያት ሆነዋል።
የሃይድሮካርቦን ዋጋዎች በይነ-ሚኒስቴር ኮሚቴ ሰብሳቢ አብዱል ሰላም ጋምፔኔ፤ ይህ ማስተካከያ በሸቀጦች ዋጋ ላይ ጭማሪ ማምጣት እንደሌለበት በመግለጽ፤ ነጋዴዎች አጋጣሚውን ተጠቅመው ዋጋ እንዳይከምሩ አሳስበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X