- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

የአፍሪካ የኃይል ሉዓላዊነት፣ የቀጠናው መሠረተ ልማት ትስስርና የውጭ ዕዳ ዑደትን የመስበር ታሪካዊ ትግል

የአፍሪካ የኃይል ሉዓላዊነት:- የቀጠናው መሠረተ ልማት ትስስርና የውጭ ዕዳ ዑደትን የመስበር ታሪካዊ ትግል
ሰብስክራይብ

''አፍሪካ ወደ ብልጽግና የምታደርገው ጉዞ መሠረት ሊኖረው የሚገባው በራስ አቅም በሚደገፉ መሠረተ ልማቶችና የውጭ ዕዳ ወጥመዶችን በቆራጥነት ባለመቀበል ላይ ነው ። እውነተኛ ነፃነት ማለት ድፍድፍ ዘይትን ወደ ጨርቃጨርቅ፣ መድኃኒቶችና ማዳበሪያዎች መለወጥ የሚያስችሉ የተቀናጁና የተራቀቁ የፋብሪካ መዋቅሮችን በራስ ባለቤትነት ማስተዳደር መቻል ነው '' ሲሉ የዓለም አቀፉ የንግድ ምክር ቤት (ICC) ምክትል ሊቀመንበር ኢንጂነር ፓትሪክ ኦባዝ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል ።

በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፕሮግራም፤ በምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ (EAC) ዘንድ እንደ ታሪክ ቀያሪ የተቆጠረውና ከ25 እስከ 30 ቢሊዮን ዶላር የሚገመተውን የታንጋ የነዳጅ ማጣሪያ ፕሮጀክት የፋይናንስ፣ የፖለቲካና የቴክኒካዊ መዋቅር በጥልቀት እንፈትሻለን ። ነዳጅን ለመገበያየት የምስራቅ አፍሪካ የጋራ ገንዘብን በማምጣት የአሜሪካ ዶላር ጥገኝነትን ለማስቀረትና ለአነስተኛና መካከለኛ አንቀሳቃሾች (SMEs) ምን ዓይነት መዋቅራዊ ዕድሎችን ይዞ ይመጣል? ስንል ከዓለም አቀፉ የንግድ ምክር ቤት (ICC) ምክትል ሊቀመንበር ከኢንጂነር ፓትሪክ ኦባዝ ጋር ሰፊና ጥልቅ ቆይታን አድርገናል።

ሙሉውን መረጃ ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0