ብሪክስ የባሕር በር አልባ አባል ሀገራትን የልማት ተግዳሮቶች ለመፍታት ያግዛል – የኢኮኖሚ ባለሙያ
20:35 06.08.2026 (የተሻሻለ: 20:44 06.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ብሪክስ የባሕር በር አልባ አባል ሀገራትን የልማት ተግዳሮቶች ለመፍታት ያግዛል – የኢኮኖሚ ባለሙያ
የባሕር በር ያላቸው እና የሌላቸው ሀገራት የብሪክስ አባል ከሆኑ፣ የአዲስ ልማት ባንክን ጨምሮ በብሪክስ የተፈጠሩ ልዩ ልዩ አሰራሮችን መጠቀም እንደሚያስችል ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ፡፡
“መሠረተ ልማቶችን ለመገንባት የሚያስፈልጉ ሀብቶችን በማግኘት የባሕር አልባ ሀገራት በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀላሉ መገበያየት እንዲችሉ ያግዛል፡፡ ሌላው ነገር ደግሞ፣ እንደሚታወቀው ብሪክስ የደቡብ-ደቡብ ትብብር ሲሆን፤ ዋና ዓላማውም በዓለም አቀፍ ደረጃ ሁለገብነትንና የጋራ ዓላማን ማበረታታት ነው።”
ባለሙያው ይህን አስተያየት የሰጡት፣ የባሕር በር አልባ ታዳጊ ሀራት ልዩ የልማት ፍላጎቶች እና ተፈታታኝ ሁኔታዎች ግንዛቤ ማስጨበጫ ዓለም አቀፍ ቀንን ምክንያት በማድረግ ነው፡፡
ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ፣ የባሕር በር አልባ ሀገራት ከብሪክስ አባልነት ሊያገኙት ስለሚችሉት ጥቀም ያብራሩበትን ቪዲዮ ይመልከቱ፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X