- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

የሕዋ ቴክኖሎጂ፣ የትምህርት እና የባህል ሉዓላዊነት፡ የአፍሪካ አዲሱ የዕድገት ምዕራፍ

የሕዋ ቴክኖሎጂ፣ የትምህርት እና የባህል ሉዓላዊነት፡ የአፍሪካ አዲሱ የዕድገት ምዕራፍ
ሰብስክራይብ
''የሕዋ ቴክኖሎጂ ልማት ለአፍሪካ ሀገራት የቅንጦት ፍላጎት ሳይሆን፣ የዲጂታል ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ፣ የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ እና የተፈጥሮ አደጋዎችን ለመከላከል በመሠረታዊነት አስፈላጊ ነው፤ ይህንንም እውን ለማድረግ በእስያ እና በአፍሪካ መካከል ያለውን የጋራ ትብብር እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማጠናከር ወሳኝ ነው'' ሲሉ የእስያ-አፍሪካ የንግድ ትስስር አማካሪ ጉንተር ባይሰል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፕሮግራማችን፤ በመጀመሪያው ክፍል እ.ኤ.አ ኦገስት 10-11/2026 የሚካሄደውን የ'አፍሪካ ዓለም አቀፍ የሕዋ ጉባኤ' (ISSA) መነሻ በማድረግ፤ የአፍሪካ የሕዋ ቴክኖሎጂ እና የሳተላይት መረጃዎችን ለሀገራት የኢኮኖሚ እድገት እና ለዲጂታል ሉዓላዊነት የመጠቀም ወሳኝ አቅምን በጥልቀት ዳስሰናል።

በሁለተኛው ክፍል ደግሞ የትምህርት ሥርዓታችንን ከውጭ ጥገኝነት በማላቀቅ የሀገር በቀል እውቀቶችን ማዕከል ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ፣ እንዲሁም የራሳችንን የፋይናንስ ሥርዓት እና የብድር ደረጃ መመዘኛ ተቋማት በመገንባት ኢኮኖሚያዊ ነፃነትን ማረጋገጥ በሚቻልበት መንገድ ላይ ከዘርፉ ከፍተኛ ምሁራን ጋር በሰፊው ተወያይተናል።

በመጨረሻው ክፍል ደግሞ የአፍሪካን ጥበብ፣ ፊልም እና የፈጠራ ስራዎች የጂኦ-ፖለቲካዊ እና የዲፕሎማሲ አቅም በማድረግ፣ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ጥላ ስር ከአለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር እኩል የመደራደር ስልታዊ መንገዶችን በስፋት ተመልክተናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ይከታተሉ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0