ሙሉ በሙሉ ሩሲያ ሠራሹ ኤምኤስ -21 የመገደኞች አውሮፕላን የመጀመሪያ የሙከራ በረራውን በስኬት አጠናቀቀ
16:42 03.08.2026 (የተሻሻለ: 16:44 03.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሙሉ በሙሉ ሩሲያ ሠራሹ ኤምኤስ -21 የመገደኞች አውሮፕላን የመጀመሪያ የሙከራ በረራውን በስኬት አጠናቀቀ
ኤምኤስ ‑21‑310 አውሮፕላን የመጀመሪያ የሙከራ በረራውን ከኢርኩትስክ አቪዬሽን ፋብሪካ በስኬት አጠናቋል ሲል የኢንዱስትሪ እና ንግድ ሚኒስቴር አስታውቋል።
አውሮፕላኑ ሙሉ በሙሉ በሩሲያ ሠራሽ አካላት የተገነባ ሲሆን ይህም ሩሲያ በሲቪል አቪዬሽን ዘርፍ በውጭ ሀገራት ምርቶች ላይ ያላትን ጥገኝነት ለመቀነስ የምታደርገውን ጥረት የሚያሳይ ትልቅ እርምጃ ነው።
የአውሮፕላኑ ዋና ዋና መግለጫዎች፦
የሚቀጥለው ትውልድ ባለ ነጠላ-መተላለፊያ፣
ከ163-211 መንገደኞችን የሚያስተናግድ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X