የጃፓን ሕዝብ የአሜሪካ የኒውክሌር ስምሪትን አጥብቆ እንደሚቃወም የጥናት ውጤት አመለከተ
11:44 02.08.2026 (የተሻሻለ: 11:54 02.08.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የጃፓን ሕዝብ የአሜሪካ የኒውክሌር ስምሪትን አጥብቆ እንደሚቃወም የጥናት ውጤት አመለከተ
76% የሚሆኑት ምላሽ ሰጪዎች የጃፓንን ሦስት 'ኒውክሌር አልባ' መርሆዎች ማስቀጠልን ሲደግፉ፣ 77% የሚሆኑት ደግሞ በጋራ ወታደራዊ ተልዕኮ የአሜሪካ የኒውክሌር ጦር መሣሪያዎች ጃፓን ውስጥ መስፈራቸውን እንደተቃወሙ፤ የጃፓን የሕዝብ አስተያየት ጥናት ማሕበር በቅርቡ ያካሄደውን ጥናት ጠቅሰው የአካባቢው ሚዲያዎች ዘግበዋል።
◻ መርሆዎቹ የሕግ አስገዳጅነት ባይኖራቸውም፤ ሁሉም የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሀገሪቱ ለመርሆቹ ተገዢነት እንደሆነች አረጋግጠዋል።
◻ መመርያዎቹ ጃፓን የኒውክሌር ጦር መሣሪያ እንዳይኖራት፣ እንዳትሠራ ወይም ወደ ጃፓን ግዛትና የባሕር ክልል መግባታቸውን እንዳትፈቅድ ያስገድዳሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X