ቻይና ሕገ-ወጥ የቢትኮይን ዝውውሮችን 90% በሚጠጋ ትክክለኛነት መከታተል የሚችል የኤአይ ሞዴል አበለፀገች

© telegram sputnik_ethiopiaቻይና ሕገ-ወጥ የቢትኮይን ዝውውሮችን 90% በሚጠጋ ትክክለኛነት መከታተል የሚችል የኤአይ ሞዴል አበለፀገች
ቻይና ሕገ-ወጥ የቢትኮይን ዝውውሮችን 90% በሚጠጋ ትክክለኛነት መከታተል የሚችል የኤአይ ሞዴል አበለፀገች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.08.2026
ሰብስክራይብ

ቻይና ሕገ-ወጥ የቢትኮይን ዝውውሮችን 90% በሚጠጋ ትክክለኛነት መከታተል የሚችል የኤአይ ሞዴል አበለፀገች

የቻይና ብሔራዊ ፖሊስ አካዳሚ ተመራማሪዎች ሕገ-ወጥ የቢትኮይን ዝውውሮችን በ89.1% ትክክለኛነት መለየት የሚችል የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ሥርዓት መገንባታቸውን የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ሥርዓቱ እንዴት ይሠራል፦

ሥርዓቱ የብሎክቼን እንቅስቃሴዎችን ለመተንተን የግራፍ ኒውራል ኔትወርክ፣ የማስታወሻ ሞጁልን እና ትልቅ የቋንቋ ሞዴልን ያጣመረ ነው።

አዳዲስ የገንዘብ ዝውውሮችን ቀደም ሲል ከተፈፀሙ ሕገ-ወጥ የገንዘብ ማጠብ ድርጊቶች ጋር በማወዳደር እየተቀየሩ የሚመጡ የወንጀል ስልቶችን ይለያል።

ጥርጣሬ ያለባቸውን የዲጂታል ገንዘብ ቦርሳዎችን ከማመልከት ባሻገር፤ ለእያንዳንዱ ጥቆማ የአደጋ ደረጃ፣ ደጋፊ ማስረጃዎችን እና ማብራሪያዎችን ያዘጋጃል።

"በኤሊፕቲክ" ይፋዊ የቢትኮይን መረጃዎች ላይ በተደረገ ፍተሻ፤ ሞዴሉ በአጠቃላይ 89.4% ትክክለኛነትን አስመዝግቧል።

ይህ ሥርዓት ቻይና በኤአይ የታገዘ የፖሊስ አገልግሎትን ለማስፋፋት የምታደርገውን ጥረት የሚያሳይ ሲሆን የብሎክቼን ምርመራዎችን ይበልጥ አውቶሜትድ፣ ግልጽ እና ወንጀለኞች ለማምለጥ የሚቸገሩበት ያደርገዋል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0