- Sputnik አፍሪካ, 1920
Continental Drift
በአፍሪካ ቅርፅ እየቀየሩ ያሉትን እንደዚሁም የደቡባዊውን ዓለም ክፍል ሚና በአዲስ መልክ እየገለጹ ያሉትን ስር ነቀል ለውጦች የሚቃኝ ፕሮግራም ነው። ትዕይንቱ ፖሊሲዎች፣ ገበያዎች እና ፈጠራዎች ከዕለት ተዕለት ሕይወት ጋር እንዴት እንደሚገናኙ በመመርመር በእውነታ ላይ የተመሰረቱ ግንዛቤዎችን እና ትክክለኛ የአፍሪካ አመለካከቶችን ያቀርባል።

ከብሉዝ እስከ ኢትዮ-ጃዝ፡ የሙዚቃ ታሪክና የአፍሪካ ድምፅ

ከብሉዝ እስከ ኢትዮ-ጃዝ፡ የሙዚቃ ታሪክና የአፍሪካ ድምፅ
ሰብስክራይብ
ሙዚቃ የባህል መገለጫ ብቻ አይደለም፤ የሰዎችን ታሪክ፣ ስቃይ፣ ተስፋ እና የኑሮ ተሞክሮ የሚያስተላልፍ ሁለንተናዊ ቋንቋ ነው። በተለይም ከአፍሪካውያን አሜሪካውያን ታሪክና ተሞክሮ የተወለደው ብሉዝ በጥቁር አሜሪካዊያ የነጻነት ትግል ውስጥ ልዩ ምልክት ሆኗል።

“ብሉዝ ለብዙ የሙዚቃ ዘውጎች መሠረት ነው። እኛም የራሳችን ብሉዝ ቢኖረንም፣ ከጥቁር ማህበረሰብ የተፈጠረው ብሉዝ ግን ለብዙ የሙዚቃ ዘውጎች መሠረት ሆኗል። ስልቱ ስሜታችንን፣ የኑሮ ሁኔታችንን፣ የሰዎችን ሀዘን እና በዓለም ላይ የሚከሰቱ ነገሮችን ሁሉ የምንገልጽበት መንገድ ነው። እነዚህ ሁሉ በብሉዝ እና በብሉዝ ተጽዕኖ በተፈጠሩ ሙዚቃዎች ውስጥ ይገለጻሉ።” ሲል ኢትዮጵያዊው የፒያኖ ተጫዋች፣ አቀናባሪ እና የኢትዮ-ጃዝ ሙዚቀኛ ሳሙኤል ይርጋ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል፡፡

በዛሬው የ"ኮንቲነንታል ድሪፍት" ዝግጅታችን፣ ዓለም አቀፍ የብሉዝ ሙዚቃ ቀንን አስመልክተን፣ ከብሉዝ እስከ ኢትዮ-ጃዝ ያለውን የሙዚቃ ትስስር፣ ታሪክ እና ባህላዊ ተፅዕኖ ከታዋቂው ፒያኖ ተጫዋችና አቀናባሪ ሳሙኤል ይርጋ ጋር እንቃኛለን።
በሁለተኛው ክፍላችን ደግሞ፣ በአዲስ አበባ የተካሄደውን "የዓለም ሕዝቦች ጉባኤ፡ አፍሪካ" በመመልከት፣ አፍሪካ የራሷን እጣ ፈንታ፣ የሀብት ሉዓላዊነት እና የጋራ የወደፊት ዕድል እንዴት መቅረጽ እንደምትችል ከምሁራን ጋር እንወያያለን።

ሙሉውን መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ይከታተሉ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripods Pocket CastsPodcast AddictCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0