- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

የአፍሪካ ሰላም በአፍሪካውያን እጅ፦ ተጠባባቂ ኃይሉን ወደ ተግባር የማሸጋገር ጥሪ

የአፍሪካ ሰላም በአፍሪካውያን እጅ፦ ተጠባባቂ ኃይሉን ወደ ተግባር የማሸጋገር ጥሪ
ሰብስክራይብ

''የአፍሪካ የጋራ ሰላምና ደህንነት ራዕይ እውን ሊሆን የሚችለው የአህጉሪቱን ችግሮች በአፍሪካውያን እቅድና አቅም መፍታት ስንችል ነው፤ አፍሪካ የሚያጋጥሟትን በርካታና ወሰን ተሻጋሪ የደህንነት ስጋቶች ሀገራት በብቸኝነት መወጣት አይችሉም። ስለዚህ የአፍሪካ ተጠባባቂ ኃይልን (Africa Standby Force) ከተቋማዊ ማዕቀፍነት ወደ ተግባራዊ የመከላከል አቅም ማሸጋገርና የራሳችንን የፋይናንስና የቴክኒክ አቅም መገንባት ከወታደራዊ ጣልቃገብነትና ጥገኝነት ለመላቀቅ ወሳኝ እርምጃ ነው'' ሲሉ በኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ የስርዓተ-ትምህርት ልማት ምክትል አዛዥ ደምሌ ሞላው (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፖድካስት፤ በመጀመሪያው ክፍል የኢትዮጵያን አህጉራዊ ጥሪ መነሻ በማድረግ የአፍሪካን ተጠባባቂ ኃይል በአፋጣኝ ወደ ሥራ ማስገባት፣ በአፍሪካ ቀንድና በምስራቅ አፍሪካ ሰላምና ደህንነትን ለማረጋገጥ ያለው አስፈላጊነት፣ የውጭ ጣልቃገብነትን የመቀነስ አቅምና ከአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 ጋር ያለውን ቁርኝት ከመከላከያ ኮሌጅ የስርዓተ-ትምህርት ልማት ምክትል አዛዥ ደምሌ ሞላው(ዶ/ር) ጋር በጥልቀት እንወያያለን። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ፤ ወደ አህጉራዊ ኢኮኖሚና የአየር ንብረት ለውጥ እውነታዎች በመሸጋገር፤ የአረንጓዴው ንቅናቄ ከውጭ የፖሊሲ ጫናዎች ተላቆ ኢኮኖሚያዊ አቅምን፣ የኃይል አቅርቦት እጥረትንና የካፒታል ፍሰት እውነታዎችን ያገናዘበ ማድረግ ስለሚያስፈልግበት ሁኔታ፤ ከቀድሞው የኢንቨስትመንት ባንከርና የኢኮኖሚክስ ባለሙያ ቮይቴክ ቦጉትስኪ ጋር ሰፊ ውይይት አድርገናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ይከታተሉ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0