"ስዋሂሊ በድንበር እና ብሔር የማይገደብ የአንድነት፣ የንግድና የባሕል ቋንቋ ነው" - የስዋሂሊ ቀን ተሳታፊዎች
15:56 01.08.2026 (የተሻሻለ: 16:04 01.08.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
"ስዋሂሊ በድንበር እና ብሔር የማይገደብ የአንድነት፣ የንግድና የባሕል ቋንቋ ነው" - የስዋሂሊ ቀን ተሳታፊዎች
"ቋንቋው በታንዛንያ የሚገኙ 120 ብሔረሰቦችን ያዋሃደ ሲሆን አሁን ደግሞ በምሥራቅ፣ ማዕከላዊ እና ደቡባዊ አፍሪካ በሚገኙ ከ14 በላይ ሀገራት እየተነገረ ይገኛል" ሲሉ በደቡብ አፍሪካ የታንዛንያ ከፍተኛ ኮሚሽነር ጄምስ ባዋና ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ቀጣዩ ደረጃ በመላው አኀጉሪቱ ቋንቋውን ለማሳደግ በአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ማዕከላትን በመክፈት፤ የስዋሂሊ ትምህርትን ከታች ጀምሮ እስከ ሙያዊ ደረጃ ተቋማዊ ማድረግ ነው ሲሉ ባዋና አክለዋል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ስዋሂሊኛን በአኀጉር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስፋፋት በሚቀጥለው ዓመት ቋንቋውን ማስተማር እንደሚጀምር የዩኒቨርሲቲው የሥነ-ጥበብ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር ሲያቦንጋ ታያሊ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
"በስዋሂሊ ቋንቋ የሚጽፉ ደራሲያን፣ የሚያስተምሩ መምህራን እና መጻሕፍት አሳታሚዎች ሊኖሩን ይገባል" ሲሉ የዓለም የስዋሂሊ ቀን ሰብሳቢ ካልቪን ሞር ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት አስተያየት አጽንኦት ሰጥተዋል።
የአፍሪካ ኀብረት ተቋማት በሁሉም መድረኮች ስዋሂሊኛን በንቃት የሚያስፋፉበት ይበልጥ የተቀናጀ አኅጉር አቀፍ አካሄድ ያስፈልጋል ሲሉ በደቡብ አፍሪካ የኡጋንዳ ከፍተኛ ኮሚሽነር ፖል አሞሩ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
"ይህ ጉዳይ በሰፊው ትኩረት አግኝቷል፤ ውጤቱም እጅግ በጣም ጥሩ እንደሚሆን እናምናለን" ሲሉ አሞሩ አክለዋል።
ከተሳታፊዎች የተሰጡ ተጨማሪ አስተያየቶችን ለመስማት የስፑትኒክ አፍሪካን ቪዲዮ ይመልከቱ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X