ሕገ-ወጥ የነዳጅ ግብይትና ሥርጭትን የሚከላከል አዲስ የዲጂታል ሥርዓት ይፋ ሆነ

© telegram sputnik_ethiopiaሕገ-ወጥ የነዳጅ ግብይትና ሥርጭትን የሚከላከል አዲስ የዲጂታል ሥርዓት ይፋ ሆነ
ሕገ-ወጥ የነዳጅ ግብይትና ሥርጭትን የሚከላከል አዲስ የዲጂታል ሥርዓት ይፋ ሆነ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 31.07.2026
ሰብስክራይብ

ሕገ-ወጥ የነዳጅ ግብይትና ሥርጭትን የሚከላከል አዲስ የዲጂታል ሥርዓት ይፋ ሆነ

 

ከጂቡቲ ተነስቶ እስከ መጨረሻው ተጠቃሚ በሚደርሰው ነዳጅ ላይ ቁጥጥር የሚያደርገውን 'ብሔራዊ የነዳጅ አቅርቦት ሰንሰለት አስተዳደር' ሥርዓት ያስተዋወቀው የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ነው።

 

ስለአዲሱ ሥርዓት ቁልፍ ነጥቦች፦

 

▪ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የበለፀገ ነው፣

▪ በጉዞ ላይ ያለ ነዳጅ እንዳይቀሸብ ይቆጣጠራል፣

▪ ለብክለት በሚዳርግ ሁኔታ እንዳይከፈት ይከላከላል፣

▪ የተጫነ ነዳጅ ቦታ ስቶ ሲሄድ በቀላሉ ለማወቅ ያስችላል።

 

ተቋሙ አሠራሩን ወደ ዲጂታል ሥርዓት ለማስገባት በሚያደርገው ጥረት፤ 29 የነዳጅ ማደያዎች ሙሉ በሙሉ 35 ደግሞ በከፊል ወደ ዘመናዊ አገልግሎት አሰጣጥ መሻገራቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ የባለሥልጣኑን ኃላፊ ጠቅሶ ዘግቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0