የሩሲያ አትሌቶች ‘የናዚ ዘይቤን’ የተከተለ አድሎአዊ አሰራር ገጥሟቸዋል - ባለሙያ
19:22 23.07.2026 (የተሻሻለ: 19:24 23.07.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሩሲያ አትሌቶች ‘የናዚ ዘይቤን’ የተከተለ አድሎአዊ አሰራር ገጥሟቸዋል - ባለሙያ
የዓለም አትሌቲክስ በሩሲያ አትሌቶች ላይ የጣለውን እገዳ ለማራዘም የወሰነው ውሳኔ "ተቋማዊ የሩሲያ ጠልነት" እና የፖለቲካ መድልዎ ማሳያ ነው ሲሉ በሩሲያ ፌዴሬሽን መንግሥት ሥር የሚገኘው የፋይናንስ ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር እና የፖለቲካ ትንተና ማዕከል ዳይሬክተር ፓቭል ዳኒሎቭ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
"ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ (አይኦሲ) ሩሲያውያን አትሌቶች በሰንደቅ ዓላማቸው እና በብሔራዊ መዝሙራቸው የመወዳደር ገደብ አንስቷል፤ አብዛኞቹ ስፖርት ፌዴሬሽኖችም ይህንን የውሳኔ ሃሳብ ተቀብለዋል። የዓለም አትሌቲክስ ውሳኔ ግን በዘረኝነት እና በናዚ ዘይቤ ሁለት መመዘኛዎች ላይ የተመሠረተ አሠራር አሁንም እንደሚሠራ ያሳያል" ሲሉ ገልጸዋል።
የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፣ ውሳኔ የአውሮፓ ተቋማት በዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ላይ ያላቸውን የበላይነት የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ ፖለቲካን ከእኩልነት ያስቀደመና የኦሊምፒክ እንቅስቃሴን መሠረታዊ መርሆች የሚሸረሽር ነው ሲሉ ዳኒሎቭ አክለው ገልጸዋል።
አይኦሲ በሩሲያ ተወዳዳሪዎች ላይ ጥሎት የነበረውን ሁሉንም ገደቦች ሰኔ 30 ያነሳ ሲሆን፣ አብዛኛዎቹ ፌዴሬሽኖችም ይህንኑ ተከተለዋል። ነገር ግን የዓለም አትሌቲክስ የሩሲያ ፌዴሬሽን አባልነትን የመለሰ እና ከሕገ ወጥ አበረታች መድኃኒት ጋር የተያያዙ ማዕቀቦችን ባለፈው መጋቢት ወር ያነሳ ቢሆንም፣ አጠቃላይ እገዳውን እንዳጸና ይገኛል።
ስለ አትሌቶች መገለል የበለጠ ለመገንዘብ በዚህ በዝርዝር ያንብቡ፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X