- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

የላቭሮቭ የአፍሪካ ጉብኝት እና የኢኮኖሚና የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ስትራቴጂ

የላቭሮቭ የአፍሪካ ጉብኝት እና የኢኮኖሚና የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ስትራቴጂ
ሰብስክራይብ
''የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ የአፍሪካ ጉዟቸውን በኢትዮጵያ ጀምረው በሳህል ቀጠና እና በሞዛምቢክ ማጠናቀቃቸው፤ ሞስኮ በባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት ላይ የተመሰረተ እውነተኛና ፍትሃዊ አጋርነትን ለመገንባት የምታደርገውን ሰፊ ስትራቴጂ በግልጽ ያሳያል'' ሲሉ ዓለም አቀፍ ግንኙነት እና የዲፕሎማሲ ምሁሩ ጥላሁን ሊበን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፖድካስት የላቭሮቭን የአፍሪካ ጉዞ መነሻ በማድረግ አህጉሪቱ ከኢኮኖሚ ጥገኝነት ለመላቀቅ እያካሄደች ያለችውን "ሁለተኛውን የነጻነት ማዕበል" እና የሩሲያ-አፍሪካ ስልታዊ አጋርነትን ከዲፕሎማሲ ምሁሩ ጥላሁን ሊበን ጋር ተወያይተናል። በክፍል ሁለት ደግሞ፣ አፍሪካ ከምዕራባውያን ማዳበሪያና የላብራቶሪ ዘሮች ጥገኝነት ወጥታ፣ በሀገር በቀል እውቀትና ሳይንሳዊ ምርምሮች ታግዛ የራሷን የምግብ ሉዓላዊነት እና የጂኦ-ፖለቲካ ጥንካሬ የምታረጋግጥበትን ወሳኝ ስልቶች ከግብርና ኤክስቴንሽን ተመራማሪው ፕሮፌሰር ዳንኤል ተመስገን ጋር በሰፊው ተወያይተናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0