- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

የላቭሮቭ የአዲስ አበባ ጉብኝት እና የሩሲያ-አፍሪካ ስትራቴጂካዊ ትብብር

የላቭሮቭ የአዲስ አበባ ጉብኝት እና የሩሲያ-አፍሪካ ስትራቴጂካዊ ትብብር
ሰብስክራይብ

''የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ጉዟቸውን በአዲስ አበባ መጀመራቸው እና ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ጋር መወያየታቸው አዲስ አበባ ለመላው አህጉር የዲፕሎማሲ ቁልፍ ማዕከል መሆኗን የሚያሳይ ከመሆኑም ባለፈ፤ ሞስኮ በባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት ላይ የተመሰረተ እውነተኛና ፍትሃዊ አጋርነትን ለመገንባት የምታደርገውን ሰፊ ስትራቴጂ በግልጽ ያሳያል።''ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲየሰላምና ደህንነት መምህርና ተመራማሪ ሙሉጌታ አየለ (ዶ/ር)ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

የዛሬው ተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፖድካስት፤ የላቭሮቭን የአዲስ አበባ ቆይታ መነሻ በማድረግ የሩሲያ አፍሪካ ስትራቴጂካዊ ግንኙነትን ከሰላምና ደህንነት ተመራማሪው ሙሉጌታ አየለ (ዶ/ር) ጋር በጥልቀት ተመልክተናል። በክፍል ሁለት ደግሞ፣ የሩሲያ ጦር በዶንባስ ግንባር የምዕራባውያን መከላከያ ምሽግ የነበረችውን ስትራቴጂካዊቷን ኮስቲያንቲኒቭካ ከተማ ነጻ ማውጣቱን ተከትሎ ይህ ክስተት በሩሲያ ልዩ ወታደራዊ ኦፕሬሽን ያለውን ትርጉምም ከአፍሪካ አንጻር በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነትና ዲፕሎማሲ መምህር እንዳለ ንጉሴ ጋር ተወያይተውናል፡፡
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0