- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

የሳህል ሀገራት ከአይሲሲ መውጣት እና የአፍሪካ የህግ ሉዓላዊነት

የሳህል ሀገራት ከአይሲሲ መውጣት እና የአፍሪካ የህግ ሉዓላዊነት
ሰብስክራይብ
''በምዕራባውያን ፈንድ ላይ ብቻ ተመስርቶ ሌሎችን ለማጥመድ የተቋቋመው የአይሲሲ (ICC) መዋቅር ወደፊት ይሻሻላል ተብሎ የሚጠበቅ አይደለም፤ በመሆኑም አፍሪካ በራሷ አቅም እና ቀጠናዊ ትስስር የፍትህ ስርዓቷን መገንባት አለባት'' ሲሉ የህግ ባለሙያው ዐምደገብርኤል አድማሱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዛሬው የቱርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፖድካስት፤ የማሊ፣ ኒጄር እና ቡርኪናፋሶ ጥምረት ከአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ለመውጣት የወሰኑትን ታሪካዊ እርምጃ መነሻ በማድረግ ከህግ ባለሙያው ዐምደገብርኤል አድማሱ ጋር ጋር በጥልቀት ተወያይተናል። አፍሪካውያን በተቋሙ መሻሻል ላይ ተስፋ በመቁረጥ ከምዕራባውያን የህግ ወጥመዶች ወጥተው፣ በገንዘብና በመዋቅር ራሱን የቻለ ቀጠናዊ የፍትህ ስርዓት ለመዘርጋት ስላላቸው አማራጭ የዲፕሎማሲ መንገዶች ተነጋግረናል።
ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0