- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

የባዮ-ኮሎኒያሊዝም ወጥመዶች እና የአፍሪካ ወጣቶች የሳይንስ ሉዓላዊነት

የባዮ-ኮሎኒያሊዝም ወጥመዶች እና የአፍሪካ ወጣቶች የሳይንስ ሉዓላዊነት
ሰብስክራይብ

''ዩኤስኤአይዲ(USAID) ከተዘጋ በኋላ ይፋ የሆኑት አዳዲስ የሁለትዮሽ የጤና ስምምነቶች፣ የአፍሪካ ሀገራት የህዝብ ጤና መረጃዎቻቸውን እና የዘረመል(ጄኔቲክ) ሀብቶቻቸውን ለውጭ አካላት ሙሉ በሙሉ አሳልፈው እንዲሰጡ የሚያስገድዱ እና ፈቃደኛ ያልሆኑትን በ180 ቀናት ውስጥ እርዳታ በማቋረጥ የሚያስፈራሩ አደገኛ የውል ወጥመዶች ናቸው'' ሲሉ የሕግ ባለሙያ እና የፖለቲካ ተንታኝ አንዷለም በእውቀቱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፖድካስት፤ በሰብአዊ እርዳታ ስም የአፍሪካን የጤና መረጃዎች፣ የዲ ኤን ኤ(DNA) መገለጫዎች እና ባዮሎጂያዊ ናሙናዎችን ለመቆጣጠር የሚደረጉ ስውር መዋቅራዊ ጫናዎችን ከሕግና ከጂኦ-ፖለቲካ እይታ አንጻር ከአንዷለም በእውቀቱ ጋር በጥልቀት ተመልክተናል። በክፍል ሁለት ደግሞ፣ አፍሪካ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ራሷን ችላ ለመቆም የምታደርገውን አስደናቂ የፈጠራ ጉዞ እንመለከታለን። በቅርቡ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ውድድር ላይ አካልን ሳይጎዳ የጭንቅላት ውስጥ ግፊትን መከታተያ ሥርዓት(CEREBRO-LOGIC) ፈጠራቸውን ይዘው ቀርበው2ኛ ደረጃን በመያዝ እውቅናን ስላገኙት የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ ሼርድ ካምፓስ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ስኬት፣ ስላጋጠሟቸው መዋቅራዊ ተግዳሮቶችና እውቀትን በባዮሜዲካል ክበባት በማጋራት ረገድ ስላላቸው የፓን-አፍሪካኒዝም መርህ ከቡድኑ አባላት ጋር በጥልቀት ተወያይተናል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple PodcastsDeezerSpotifyAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0