ሩሲያ አሠናካይ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን የሚቋቋም አዲስ የድሮን መገናኛ ሥርዓት ይፋ አደረገች
19:40 30.06.2026 (የተሻሻለ: 19:44 30.06.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ አሠናካይ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን የሚቋቋም አዲስ የድሮን መገናኛ ሥርዓት ይፋ አደረገች
ሮስቴክ በኤሌክትሮኒክስ ጦርነት ወቅት የሚፈጠሩ የሞገድ አጨናጋፊዎችን መቋቋም የሚችል አዲስ የድሮን መገናኛ ሥርዓት አልምቷል።
የሥርዓቱ ዋና ዋና ጠቀሜታዎች፡-
አስተማማኝ የዕዝ፣ የቴሌሜትሪ እና የቪዲዮ ስርጭትን ያረጋግጣል።
በቻናሎች መካከል ፈጣን ሽግግር በሚያደርግበት ወቅት የመረጃ ፍጥነትን እና ፍሪኩዌንሲን በቅጽበት ይለውጣል — ይህም የጠላት የሞገድ ማናወዣዎች ሥርዓቱን እንዳያፍኑት ያደርጋል።
ፍሪኩዌንሲዎችን በመቀያየር ራሱን ከሚሰነዘርበት የጃሚንግ ጥቃት ጋር በቅጽበት ያስማማል።
ይህ አዲስ የቴክኖሎጂ ልማት ድሮኖች የጠላትን የመከላከል እርምጃዎች የመቋቋም አቅማቸውን ለማሻሻል እየተደረገ ያለውን ቀጣይ ጥረት ያሳያል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X