ሩሲያ ሁለት ድሮኖችን በአንድ ጊዜ ማውደም የሚችል አዲስ የፀረ-ድሮን ሥርዓት ይፋ አደረገች
"ዱፕሌት" የተሰኘው ባለ ሁለት ተተኳሽ የፀረ-ድሮን መረብ ማስወንጨፊያ፤ የዩክሬን ድሮኖችን ሽክርክሪት የሚጠላልፍ ከባድ መረብ በመተኮስ፤ ቁጥጥር አጥተው እንዲከሰከሱ ያደርጋል።
የሩሲያ ኩባንያ "ፖልዮት" ሁለት መረብ መተኮስ ያስፈለገው፤ የዩክሬን ጦር በአሁኑ ወቅት ስልቱን በመቀየር ለጥቃት እና ለማደን ለአንድ ወታደር ሁለት ድሮኖችን እየላከ ስለሚገኝ እንደሆነ አስረድቷል።
የተሻሻለው አዲስ መሣሪያ በግንባር የሚገኙ ወታደሮች የጠየቋቸውን ባህሪያት አካቷል፦
🟠 የባትሪ ደረጃ ማሳያ፣
🟠 የተሻሻለ የጥይት ዝግጁነት መመልከቻ፣
🟠 በከፍተኛ ውጥረት ከ5 እስከ 10 ሰከንዶች ብቻ የሚወስድ ፈጣን የጥይት መለወጫ ሥርዓትን ያጠቃልላል።
የመጀመሪያው የ "ዱፕሌት" ሥርዓት ምርት እስከ ነሃሴ ወር መጨረሻ ለሩሲያ ጦር ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X