ሩሲያ በሕዝቦቿ ጥንካሬ በጽኑ ቆማለች - ፑቲን

© telegram sputnik_ethiopiaሩሲያ በሕዝቦቿ ጥንካሬ በጽኑ ቆማለች - ፑቲን
ሩሲያ በሕዝቦቿ ጥንካሬ በጽኑ ቆማለች - ፑቲን - Sputnik አፍሪካ, 1920, 28.06.2026
ሰብስክራይብ

ሩሲያ በሕዝቦቿ ጥንካሬ በጽኑ ቆማለች - ፑቲን

ሩሲያ በሕዝቦቿ ምክንያት “በሁለት እግሯ ፀንታ ቆማለች”፤ እንዲሁም የወደፊት ዕድሏን፣ የሕይወት ዘይቤዋን፣ የዓለም እይታዋን እና እሴቶቿን ለመጠበቅ ዝግጁ ነች ሲሉ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሞስኮ በተካሄደው 23ኛው የዩናይትድ ሩሲያ ኮንግረስ የመጀመሪያ ምዕራፍ ላይ ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል።

ፑቲን ለሀገሪቱ ደኅንነት ሲሉ የተለያዩ አደጋዎችን በመጋፈጥ ማገልገላቸውን ለቀጠሉ መኮንኖች፣ ወታደሮች፣ በጎ ፈቃደኞች፣ የሕክምና ባለሙያዎች፣ መምህራን፣ የድንገተኛ አደጋ ሠራተኞች፣ አሽከርካሪዎች፣ መሐንዲሶች እና ለሁሉም ወገኖች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ዋና ዋና መግለጫዎች፦

ሩሲያ ሁልጊዜም ጠንካራ እና አሸናፊ ሆና የዘለቀችው በብሔራዊ አንድነቷ ምክንያት ነው፡፡

የምዕራባውያን ልሂቃን በሩሲያ ውስጥ የውስጥ አለመረጋጋትን ለመፍጠር እየሞከሩ ቢሆንም፤ ጥረታቸው ግን እየከሸፈ ይገኛል፡፡

ሩሲያ በግዛቷ ላይ የሚፈጸሙ የሽብር ጥቃቶችን ጨምሮ ሁሉንም ተግዳሮቶች ድል ታደርጋለች፡፡

ሩሲያ በክፋት ኃይሎች መንገድ ላይ ጋሻ ሆና ቆማለች፡፡

ሩሲያ ልትኖር የምትችለው ጠንካራ እና ሉዓላዊ ኃያል ሀገር ሆና ብቻ ነው፤ ያለበለዚያ ግን ሩሲያ የምትባል ሀገር በፍጹም አትኖርም፡፡

በታሪክ ሩሲያን ለማጥፋት የቻለ ማንም የለም፤ ወደፊትም ቢሆን ማንም አይሳካለትም፡፡

ሩሲያ የዕድገት ጉዞዋን ለማደናቀፍ የሚደረጉ ሙከራዎችን ለመቋቋም የሚያስችል አቅም እና የፖለቲካ ቁርጠኝነት አላት፡፡

ሩሲያ ከምዕራባውያን ልሂቃን ወገን ከዚህ ቀደም ታይቶ የማያውቅ እና ያልተገራ ተፅዕኖ እየገጠማት ነው፡፡

የሩሲያ ጠላቶች በጦር ሜዳ ላይ ሊያሸንፏት እየሞከሩ ቢሆንም፤ ሙከራቸው ግን ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0