ናይሮቢ ከጄን-ዚ ተቃውሞ መታሰቢያ ዋዜማ በፊት በከፍተኛ ጥንቃቄ ላይ ትገኛለች - ዘጋቢ

ሰብስክራይብ

ናይሮቢ ከጄን-ዚ ተቃውሞ መታሰቢያ ዋዜማ በፊት በከፍተኛ ጥንቃቄ ላይ ትገኛለች - ዘጋቢ

  እ.ኤ.አ. ሰኔ 25 ቀን 2024 የተካሄደውን የፋይናንስ ረቂቅ አዋጅ ተቃውሞ ሁለተኛ ዓመት መታሰቢያ ለማድረግ ከታቀዱ ሰልፎች አስቀድሞ፤ በኬንያ የፓርላማ ሕንጻዎች ዙሪያ ከፍተኛ የፀጥታ ኃይል መሰማራቱን የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል።

🟠 ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆነ የፀረ-አመፅ ፖሊሶች እና ሌሎች የፀጥታ አካላት በፓርላማ መንገድ ላይ የተሰማሩ ሲሆን፤ በቁልፍ የመንግሥት ተቋማት ዙሪያ በአደገኛ የሽቦ አጥር የታጠሩ የደኅንነት ኬላዎች ተዘርግተዋል፤ እንዲሁም በናይሮቢ ማዕከላዊ የንግድ ዲስትሪክት በከፊል ወደ ውስጥ የሚገቡ መንገዶች ተገድበዋል፤

🟠 በበርካታ መንገዶች ላይ የፖሊስ የፍተሻ ጣቢያዎች መኖራቸውና የትራፊክ መስተጓጎል መፈጠሩ የተነገረ ሲሆን፤ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ወደ ማዕከላዊ የንግድ ዲስትሪክቱ እንዳይገቡ በመከልከላቸው ምክንያት አንዳንድ የንግድ ቤቶች ተዘግተዋል፣ ተጓዦችም በእግራቸው ለመጓዝ ተገድደዋል፤

🟠 ባለሥልጣናቱ እንደገለጹት፤ እነዚህ እርምጃዎች የመንግሥት ተቋማትን ለመጠበቅ እና የሕዝብን ሰላምና ጸጥታ ለማስከበር የታለሙ ናቸው።

ይህ የመታሰቢያ መርሃ-ግብር እየተከናወነ ያለው፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣት ተቃዋሚዎች የፓርላማውን ቅጥር ግቢ ጥሰው በመግባት ግጭቶች፣ የሰዎች ሕይወት መጥፋት፣ የአካል ጉዳት እና ከፍተኛ የፖለቲካ ቀውሶች ካስከተለው ተቃውሞ ከሁለት ዓመታት በኋላ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia
ናይሮቢ ከጄን-ዚ ተቃውሞ መታሰቢያ ዋዜማ በፊት በከፍተኛ ጥንቃቄ ላይ ትገኛለች - ዘጋቢ - Sputnik አፍሪካ
1/2
© telegram sputnik_ethiopia
ናይሮቢ ከጄን-ዚ ተቃውሞ መታሰቢያ ዋዜማ በፊት በከፍተኛ ጥንቃቄ ላይ ትገኛለች - ዘጋቢ - Sputnik አፍሪካ
2/2
1/2
2/2
አዳዲስ ዜናዎች
0