አልጄሪያ ለኒጀር የሕክምና ዘርፍ ሙያዊ ድጋፍ ልትሰጥ እንደሆነ አስታወቀች

ሰብስክራይብ

አልጄሪያ ለኒጀር የሕክምና ዘርፍ ሙያዊ ድጋፍ ልትሰጥ እንደሆነ አስታወቀች

​የኒጀር የጤና ሚኒስትር ጋርባ ሃኪሚ ከአልጄሪያ አቻቸው መሐመድ ሲዲክ አይት መሳውዳን ጋር በአልጀርስ ባደረጉት ውይይት፤ አልጀርስ የኒያሜን የጤና መሠረተ ልማት ለማልማትና ለማጠናከር ቃል ገብታለች።

በውይይቱ የተደረሱ ዋና ዋና ስምምነቶች፦

​🟠 አልጄሪያ፤ የኒጀርን የኩላሊት እጥበት ማዕከል በመገንባት፣ መሣሪያ በማደራጀት እና የሕክምና ስፔሻሊስቶችን በማሠልጥን ድጋፍ ታደርጋለች።

​🟠 ከኒጀር የቅድመ-መከላከልና ጤና ግንባታ አጠቃላይ ዳይሬክቶሬት እንዲሁም ከአልጄሪያ ፓስተር ኢንስቲትዩት ጋር በመቀናጀት፤ የወረርሽኝ መከላከልና ቁጥጥር ማዕከል እንዲቋቋም አልጄሪያ የበኩሏን ታግዛለች።

​🟠 ሁለቱ ወገኖች ድንበር ተሻጋሪና ተላላፊ በሽታዎችን አስቀድሞ መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያም ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0