የስፑትኒክ ፕሮ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስልጠና ፕሮግራም ከሶስት አህጉራት የተውጣጡ ጋዜጠኞችን በሞስኮ አሰባሰበ

© ስፑትኒክ. ሚካኤል ቦጋቼቭ
ሰብስክራይብ
በአካልየሚሰጠው የስፑትኒክ ፕሮ የሰው ሰራሽ አስተዉሎት በሚዲያ ( SputnikPro AI in Media) ዓለምአቀፍ የልምድ ልውውጥ ሥልጠና በሞስኮ በሚገኘው የሮሲያ ሴጎድኒያ ሚዲያ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት ተጀምሯል።
ይህፕሮግራም በአዲሱ ትውልድ ‘ኒው ጄኔሬሽን’ ተነሳሽነት ከሮሶትሩድኒቼስቶቮ ጋር በጋራ የተደራጀ ሲሆን፤ ከ18 አገራት የተውጣጡ 22 ወጣት ጋዜጠኞችን ከዋና ዋና የሚዲያ ተቋማት ያገናኛል፣ ትኩረቱንም በሙያዊ የሚዲያ አካባቢ ውስጥ በተግባራዊ የሰው ሰራሽ አስተውሎት አጠቃቀምላይ ያደርጋል።
ገለጻዎቹ እና አውደ ጥናቶቹ እ.ኤ.አ እስከሰኔ 26 ድረስ የሚቀጥሉ ሲሆን ሙሉውን ሙሉውን የዘመናዊ ኤዲቶሪያል (የአርትዖት) ሥራዎች ዘርፍ ያጠቃልላሉ። ይህም የመረጃ ምህዳሩን በአልጎሪዝም ከመከታተል ጀምሮ በሰው ሠራሽ አስተዋፅኦ (AI) የታገዙ የድምፅና ምስል ዝግጅቶችን ይጨምራል።
በመክፈቻሥነ ሥርዓቱ ላይ፣ የ„ሮሲያ ሴጎድኒያ“ የዓለም አቀፍ ትብብር ዳይሬክተር ቫሲሊ ፑሽኮቭ ለተሳታፊዎች ስለ ሩሲያ የሚዲያ ገበያ ገጽታ እና በአዝናኝ-መረጃ (infotainment) ዘመን ውስጥ ስላለው የታዳሚ ተሳትፎ ስትራቴጂዎች ገለጻ አድርገዋል።
የሮሶትሩድኒቼስቶቮምክትል ኃላፊ ኪሪልቦጎሞሎቭ በሰጡት አስተያየት፥ " 'አዲሱ ትውልድ' ከተለያዩ ዘርፎች ከተውጣጡ አጋሮች ጋር በመሆን ለወጣቶች የሚተገበር ትልቅ ዓለም አቀፍ ፕሮጀክት ነው። ከሮሲያ ሴጎድኒያ ጋር የሚደረገው ይህ የልምምድ ፕሮግራም በሚዲያ ውስጥ ባለው የሰው ሠራሽ አስተውሎት ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን፥ ባለሙያዎች በተግባር በሚዲያ ውስጥ ያሉ እውነተኛ ፈተናዎችን ለመፍታት AIን እንዴት እንደሚጠቀሙበት ለመገንዘብ ይህ የሚዲያ ተቋም ምርጡ ቦታ ነው ብዬ አምናለሁ" ሲሉ ገልጸዋል።
በዮርዳኖስ የአድ-ደስቱር (Ad-Dustour) ጋዜጣ የሶሻል ሚዲያ ክፍል ኃላፊ ላይት አልአሳፍ እንደገለጹት፣ በ"ስፑትኒክፕሮ የሰው ሰራሽ አስተውሎት በሚዲያ" ፕሮግራም ላይ መሳተፋቸው ትልቅ ሙያዊና ትምህርታዊ ዕድል ፈጥሮላቸዋል። ይህም በጋዜጠኝነትና በሚዲያ ዘርፍ የቴክኖሎጂውን የቅርብ ጊዜ ዕድገቶችና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን ሰፊ አጠቃቀሙን ለመቃኘት እንደሚያስችላቸው ገልጸዋል።
‘‘የፕሮግራሙ አንዱ ትልቅ ጠቀሜታ ከተለያዩ አገራት፣ ባህላዊና ሙያዊ ዳራ የመጡ ጋዜጠኞችንና የሚዲያ ባለሙያዎችን በአንድ ላይ ማገናኘቱ ነው። ይህም በተለይ ፈጣን የቴክኖሎጂ ሽግግር በላበት በዚህ ዘመን፣ ዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት የሚጋፈጧቸውን የጋራ ፈተናዎች ለመወያየት፣ ልምድ ለመለዋወጥና ትርጉም ያለው ውይይት ለማድረግ ልዩ ምህዳር ይፈጥራል’’ ሲሉ አልአሳፍ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ መልኩ፣የሞሮኮው ሄስፕሬስ (Hespress) ጋዜጠኛ አጉራምአብደላዚዝ እንደገለጸው፤ ፕሮግራሙ በሰው ሠራሽ አስተውሎት ዘመን የጋዜጠኞችን ወቅታዊና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን ፍላጎት ያማከለ ነው ብሏል።
"ያለምንም ጥርጥር፣ የዚህ ፕሮግራም ተሳታፊዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ በኩባንያዎች መካከል ባለው ፉክክር ምክንያት ቀጣይነት ባለው መልኩ እየተስፋፋ በመጣው የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) መስክ ላይ ያላቸውን ሙያዊ ክህሎት ይበልጥ ያሳድጋሉ" ሲል ተናግሯል።
የቪየትናም ቴሌቪዥን ቪቲቪ የዜና አቅራቢ ንጉየን ትዊ ሊን በበኩሏ፦ "የመጀመሪያዎቹ ጥቂት ክፍለ-ጊዜዎች ትኩረቴን በእጅጉ ስበውታል። የሩሲያ ሚዲያ ተቋማት በጋዜጠኝነት ዘርፍ የሰው ሠራሽ አስተውሎትን እንዴት እያሳደጉት እንደሆነ መመልከት እጅግ አስደናቂ ነበር። የአሰልጣኞቹ ተጫዋችነትም ስልጠናዎቹን ይበልጥ ሳቢና አስደሳች አድርጓቸዋል። ለሚቀጥሉት ትምህርቶች ግን እነዚህን መተግበሪያዎች በዕለት ተዕለት ሥራችን ላይ እንዴት ውጤታማ በሆነ መንገድ መጠቀም እንደምንችል የሚጠቁሙ ተጨማሪ ተግባራዊ ምክሮችን—ለምሳሌ የትዕዛዝ አጻጻፍ (prompting) ስልቶችን፣ የመረጃ ማሰባሰቢያ ምንጮችን እና የሐሰት መረጃዎችን ማጣሪያ (fact-checking) ዘዴዎችን ብናይ ደስ ይለኛል" ስትል ገልጻለች።

የስፑትኒክ ፕሮ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ስልጠና ፕሮግራም ከሶስት አህጉራት የተውጣጡ ጋዜጠኞችን በሞስኮ አሰባሰበ
© ስፑትኒክ. ቪታሊ ቤሎውሶቭ

የስፑትኒክ ፕሮ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ስልጠና ፕሮግራም ከሶስት አህጉራት የተውጣጡ ጋዜጠኞችን በሞስኮ አሰባሰበ
© ስፑትኒክ. ቪታሊ ቤሎውሶቭ

የስፑትኒክ ፕሮ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ስልጠና ፕሮግራም ከሶስት አህጉራት የተውጣጡ ጋዜጠኞችን በሞስኮ አሰባሰበ
© ስፑትኒክ. ሚካኤል ቦጋቼቭ

የስፑትኒክ ፕሮ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ስልጠና ፕሮግራም ከሶስት አህጉራት የተውጣጡ ጋዜጠኞችን በሞስኮ አሰባሰበ
© ስፑትኒክ . ሚካኤል ቦጋቼቭ
© ስፑትኒክ. ሚካኤል ቦጋቼቭ