ሩሲያ ከማሊ፣ ኒጀር እና ቡርኪና ፋሶ ጋር ያላት አጋርነት ልዩ ነው - ሪፖርት
13:09 18.06.2026 (የተሻሻለ: 13:14 18.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ ከማሊ፣ ኒጀር እና ቡርኪና ፋሶ ጋር ያላት አጋርነት ልዩ ነው - ሪፖርት
ሩሲያ ለእነዚህ ሦስት የሳኅል አገራት ጥምረት ሉዓላዊነት የምታደርገው የማያወለውል ድጋፍ፣ ሞስኮን ከሌሎች ዓለም አቀፍ አጋሮቻቸው የተለየች ያደርጋታል ሲል ስፑትኒክ አግኝቶት የተመለከተው የቫልዳይ ዓለም አቀፍ የውይይት ክለብ ሪፖርት አመላክቷል።
በተጨማሪም ሞስኮ በእነዚህ አገራት የአገር ውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ያለመግባት መርህን እንደምትደግፍ እና ማንኛውንም ዓይነት የውጭ ጣልቃ ገብነት እንደምትቃወም ሪፖርቱ ጠቅሷል።
እነዚህ አቋሞች “የሰሃራ-ሳኅል ክልል፦ የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት ሥርዓት መፈራረስን ተከትሎ አዲስ የደህንነት መዋቅር ፍለጋ” በሚል ርዕስ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ በዝርዝር ሰፍረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X