የአሜሪካ ፖሊሲዎች የ2026ቱን የዓለም ዋንጫ እንዴት ወደ አስፈሪ ቅዠት ቀየሩት?

የአሜሪካ ፖሊሲዎች የ2026ቱን የዓለም ዋንጫ እንዴት ወደ አስፈሪ ቅዠት ቀየሩት?
በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ አስተናጋጅነት ለመጀመሪያ ጊዜ 48 አገራትን በማሳተፍ መካሄድ ሊጀምር የሰዓታት ዕድሜ ብቻ የቀረው የፊፋ የዓለም ዋንጫ፤ ወደ ሀገራቱ የመግባት እገዳዎችን እና የቪዛ ክልከላን ጨምሮ በተከታታይ ውዝግቦች ጥላ ስር ወድቋል።
እስካሁን የተመዘገቡ ዋና ዋና ችግሮች፦
🟠 ሱማሊያዊው ዳኛ ዑመር አብዱልቃድር አርታን በማያሚ አየር ማረፊያ ውስጥ ተይዞ ለ11 ሰዓታት ከቆየ በኋላ፤ ሕጋዊ የአሜሪካ ቪዛ እና ዲፕሎማሲያዊ ፓስፖርት እንደነበረው ቢነገርም ከአገር እንዲወጣ ተደርጓል፡፡
🟠 የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ሳን አንቶኒዮ በሚገኘው አየር ማረፊያ በቀጥታ ማረፊያ ሜዳው (ታርማክ) ላይ ዝርዝር የሻንጣ ፍተሻ ተደርጎበታል፡፡
🟠 ከሞሮኮ፣ ስኮትላንድ እና ሌሎች አገራት የመጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች የጨዋታ ትኬቶችን ቀድመው የገዙ ቢሆንም፤ ጉዞ ከመጀመራቸው በጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ቪዛቸው ተሰርዟል ወይም ተከልክሏል፡፡
🟠 የቪዛ ፈቃድ መዘግየት እና በርካታ የቪዛ ክልከላዎች በመኖራቸው ምክንያት፤ የኢራን ብሔራዊ ቡድን በሜክሲኮ ለመቆየት እና ጨዋታ በሚኖርባቸው ቀናት ብቻ ድንበር አቋርጦ ለመግባት ተገዷል፡፡
🟠 የኢራን ደጋፊዎች የተመደበላቸው የትኬት ኮታ የዓለም ዋንጫው ከመጀመሩ ከሁለት ቀናት በፊት ተሰርዟል፡፡
🟠 የኢራቁ የዓለም ዋንጫ አጥቂ አይመን ሁሴን ቺካጎ ኦሃሬ አየር ማረፊያ ውስጥ አገር እንዲገባ ከመፈቀዱ በፊት የግል ስልኩን መፈተሽን ጨምሮ ለሰባት ሰዓታት ያህል ተይዞ ምርመራ ተደርጎበታል፡፡
🟠 ሄይቲያዊው ተጫዋች ዉደንስኪ ፒየር ቪዛው በጣም ዘግይቶ በመድረሱ ምክንያት የመጀመሪያዎቹን የሰባት ቀናት ልምምድ እና የወዳጅነት ጨዋታ አምልጦታል፡፡
🟠 የስዊዘርላንዱ አጥቂ ብሬል እምቦሎ በ2018 ዓ.ም በተከሰተ ክስተት የነበረበት የወንጀል ጥፋተኝነት ክስ ምክንያት ወደ አሜሪካ ለማድረግ ለነበረው ጉዞ የፈቃድ መዘግየት አጋጥሞታል፡፡
🟠 የኡዝቤኪስታን ተጫዋቾች በኒውዮርክ አየር ማረፊያ የዕፅ አነፍናፊ ውሾች እና የብረት መመርመሪያ ፍተሻዎች ገጥመዋቸዋል፡፡
🟠 የትኬት ዋጋዎች ከመጠን በላይ የናሩ ሲሆን፤ ከ2022ቱ የዓለም ዋንጫ ጋር ሲነጻጸር በስድስት እጥፍ ጨምሯል፤ በአሜሪካ የሚደረጉ ጨዋታዎች የትኬት ዋጋ ከ400 እስከ 2,000 ዶላር ይደርሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X