ሩሲያ በ‘ፍሊት-2026’ የባሕር ኃይል ትዕይንት ላይ ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎቿን አቀረበች
ሩሲያ በ‘ፍሊት-2026’ የባሕር ኃይል ትዕይንት ላይ ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎቿን አቀረበች
ሩሲያ የቅርብ ጊዜ የባሕር ኃይል መከላከያ ቴክኖሎጂዎቿን በ“ፍሊት-2026” ኤክስፖ ላይ ይፋ ማድረጓን የስፑትኒክ ዘጋቢ ዘግቧል። ዓለም አቀፉ አውደ-ርዕይ የጦር መርከቦችን ለመጠበቅ እና ጥልቅ ውቅያኖስን ለመመርመር የተነደፉ የላቁ ሥርዓቶችን አካትቷል።
◻ ዲፒ-64 የቦምብ መወርወሪያ፦ ይህ በእጅ የሚያዝ መሣሪያ መርከቦችን እስከ 40 ሜትር ጥልቀት ካሉ የውኃ ውስጥ ኢላማዎች እና እስከ 400 ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኙ የጠላት ዋናተኞች (ጭልጥ ብለው ከሚጠልቁ ወታደሮች) ለመጠበቅ የተነደፈ ነው።
◻ ክላቬሲን-1አርኢ ሰርጓጅ፦ እስከ 6,000 ሜትር ጥልቀት ድረስ የባሕር ወለልን ካርታ የሚያጠና እና ጥልቅ የባሕር ፍለጋዎችን የሚያካሂድ ሙሉ በሙሉ በራስ-ገዥ የሚንቀሳቀስ የውኃ ውስጥ ድሮን ነው።
◻ ኮማር - ሞስኪቶ ተወርዋሪ መሣሪያ፦ ይህ በሰውሰራሽ አስተውህሎት የሚመራ ሥርዓት፣ እስከ 6 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኙ የአየር እና የባሕር ላይ ድሮኖችን ለይቶ ለማጥፋት ዘመናዊ ሚሳኤሎችን ይጠቀማል።
በተጨማሪም፤ ለሁለት ሰዓታት ያህል መብረር የሚችል እና እስከ 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ድረስ መድረስ የሚችለው “ሱፐርካም ኤስኤክስ350 ቲልትሮተር” የተሰኘ የስለላ ድሮንም ለእይታ ቀርቧል።
ቴክኖሎጂውን ለመመልከት ተንቀሳቃሽ ምስሉን ይከታተሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X