አንድ አካል ሁለት አምሳል፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላን በናይጄሪያ አየር መንገድ አርማና ቀለም ገፀ ቅብ ለዕይታ ቀርቦ እንደነበር ተሰማ

© telegram sputnik_ethiopiaአንድ አካል ሁለት አምሳል፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላን በናይጄሪያ አየር መንገድ አርማና ቀለም ገፀ ቅብ ለዕይታ ቀርቦ እንደነበር ተሰማ
አንድ አካል ሁለት አምሳል፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላን በናይጄሪያ አየር መንገድ አርማና ቀለም ገፀ ቅብ ለዕይታ ቀርቦ እንደነበር ተሰማ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 11.06.2026
ሰብስክራይብ

አንድ አካል ሁለት አምሳል፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላን በናይጄሪያ አየር መንገድ አርማና ቀለም ገፀ ቅብ ለዕይታ ቀርቦ እንደነበር ተሰማ

የቀድሞው የናይጄሪያ አቪዬሽን ሚኒስትር ሃዲ ሲሪካ ከ2 ቢሊዮን ናይራ በላይ የህዝብ ገንዘብ አባክነዋል በሚል በቀረበባቸው ክስ ትናንት ረቡዕ በነበረ የፍርድ ቤት ውሎ አስገራሚ ምስክርነት ተሰምቷል።

እ.ኤ.አ በ2023 የናይጄሪያ አየር መንገድ (Nigeria Air) ፕሮጀክት ተጠናቆ ሥራ ሊጀምር ነው ተብሎ በታላቅ ድምቀት ለህዝብ እይታ የቀረበው አውሮፕላን፣ በወቅቱ በኪራይ የመጣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን እንደነበር የደህንነት መሥሪያ ቤቱ ምስክር ለፍርድ ቤት አረጋግጧል።

የናይጄሪያ አየር መንገድ አርማና ቀለም የተቀባው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው አውሮፕላን፣ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ሥልጣን ከመልቀቃቸው 3 ቀናት ቀደም ብሎ አቡጃ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሶ ነበር።

አውሮፕላኑ ለጥቂት ቀናት ለዕይታ ብቻ ከቆመ በኋላ፣ የተቀባው ቀለምና አርማ ተፍቆ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞች እየበረረ ወዲያውኑ ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል።

ሚኒስትሩ ይህን ፈጽመዋል የተባሉት የሥልጣን ዘመናቸው ከማብቃቱ በፊት "የአየር መንገድ ፕሮጀክቱን አሳክቻለሁ" ለማለት እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ በቀጣይ የፍርድ ቤቱ ቀጠሮ በሚኒስትሩ ድምፅ የተቀረጸ የድምፅ ማስረጃ በፍርድ ቤት እንደሚደመጥ የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0