የኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማኅበር የቤት ሽያጭ ዋጋን በግንባታ ወጪ ላይ ለመመሥረት ጥናት እያካሄደ መሆኑን አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopiaየኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማኅበር የቤት ሽያጭ ዋጋን በግንባታ ወጪ ላይ ለመመሥረት ጥናት እያካሄደ መሆኑን አስታወቀ
የኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማኅበር የቤት ሽያጭ ዋጋን በግንባታ ወጪ ላይ ለመመሥረት ጥናት እያካሄደ መሆኑን አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 11.06.2026
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማኅበር የቤት ሽያጭ ዋጋን በግንባታ ወጪ ላይ ለመመሥረት ጥናት እያካሄደ መሆኑን አስታወቀ

ጥናቱ የሪል ስቴት ኩባንያዎች ቤት ለቤት ግንባታ ያወጡትን ወጪ መሠረት ያደረገ አማካይ የሽያጭ ዋጋ ተመን እንዲኖራቸው የሚያስችል መሆኑን ማሕበሩን ጠቅሶ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ ኢንጂነር ዝናቡ ተበጀ፣ በአሁኑ ወቅት በገበያው ውስጥ በካሬ ሜትር ከ50 ሺህ እስከ 400 ሺህ ብር የሚሸጡ ቤቶች ያሉ ሲሆን፣ ጥናቱ የማርኬቲንግ፣ የፋይናንስ፣ የታክስ እና የመሬት ክፍያን ጨምሮ አጠቃላይ የግንባታ ወጪን መሠረት ያደረገ ወጥ አማካይ ዋጋ ለመተመን ያስችላል ብለዋል።

ይህ አሰራር ገዢዎች ዋጋው “ረካሽ ነው” በሚል ብቻ ተታለው በመግዛት ለከፍተኛ ኪሳራ እንዳይዳረጉ የሚከላከል ከመሆኑም በላይ፣ ኩባንያዎች የሌሎችን ተጽዕኖ ሳይጠብቁ የራሳቸውን ወጪ መነሻ አድርገው እንዲተምኑ እና የአካባቢው መሰረተ ልማት መሟላት (እንደ ትምህርት ቤትና ጤና ተቋማት መኖር) ታሳቢ ተደርጎ ተጨማሪ የዋጋ መለኪያዎች እንዲወጡ ያግዛል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0